Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




መሳፍንት 20:47 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

47 ነገር ግን ስድስት መቶ ሰዎች ወደ ሁላ ዙረው በምድረ በዳው ውስጥ ወዳለው ወደ ሬሞን ዐለት ሸሹ፤ በዚያም አራት ወር ተቀመጡ።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

47 ነገር ግን ስድስት መቶ ሰዎች ጀርባቸውን አዙረው በምድረ በዳው ውስጥ ወዳለው ወደ ሬሞን ዐለት ሸሹ፤ በዚያም አራት ወር ተቀመጡ።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

47 ነገር ግን ወደ በረሓው፥ የሪሞን አለት ተብሎ ወደሚጠራው ስፍራ በመሸሽ ለማምለጥ የቻሉት ስድስት መቶ ሰዎች ብቻ ነበሩ። እነርሱም በዚያ አራት ወር ቈዩ።

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

47 ስድ​ስ​ቱም መቶ ሰዎች ተመ​ል​ሰው ወደ ምድረ በዳ ወደ ሬሞን ዓለት ሸሹ፤ በሬ​ሞ​ንም ዓለት አራት ወር ተቀ​መጡ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

47 ስድስቱም መቶ ሰዎች ተመልሰው ወደ ምድረ በዳ ወደ ሬሞን ዓለት ሸሹ፥ በሬሞን ዓለት አራት ወር ተቀመጡ።

See the chapter Copy




መሳፍንት 20:47
9 Cross References  

ጌታ ሆይ፥ ዝናህን ሰምቻለሁ፥ በሥራህም ጌታ ሆይ ፈራሁ፥ በዓመታት መካከል አድሰው፥ በዓመታት መካከል አስታውቀው፥ በቁጣ ጊዜ ምሕረትን አስብ።


ቢያሳዝንም እንደ ምሕረቱ ብዛት ይራራልና፥


“ኃጢአታችን ብዙ ነውና፥ በአንተም ላይ ኃጢአትን ሠርተናል፤ ምንም እንኳ ኃጢአታችን ቢመሰክርብንም ስለ ስምህ ብለህ አቤቱ! አድርግ።


የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ዘርን ባያስቀርልን ኖሮ፤ እንደ ሰዶም በሆንን ገሞራንም በመሰልን ነበር።


ከዚያም ጉባኤው በሙሉ በሬሞን ዐለት ወዳሉት ብንያማውያን የሰላም ጥሪ አስተላለፈ።


በዚያች ዕለት ሰይፍ የታጠቊ ሃያ አምስት ሺህ ብንያማውያን በጦር ሜዳ ወደቊ፤ ሁሉም ምርጥ ተዋጊዎች ነበሩ።


ከዚያም እስራኤላውያን ወደ ብንያም ምድር ተመልሰው ከተሞቻቸውን በሙሉ እንዲሁም እንስሳቱንና በዚያ ያገኙትን ሁሉ በሰይፍ መቱ፤ በመንገዳቸው ያገኙትን ከተማ ሁሉ በእሳት አቃጠሉ።


ምድር ሁሉ ከጌባ ጀምሮ በኢየሩሳሌምም ደቡብ በኩል እስካለችው እስከ ሬሞን ድረስ ተለውጣ፥ እንደ ዓረባ ትሆናለች፤ እርሷም ከፍ ከፍ ትላለች፥ ከብንያምም በር ጀምሮ እስከ ፊተኛው የበሯ ስፍራ እስከ ማዕዘኑ በር ድረስ፥ ከሐናንኤልም ግንብ ጀምሮ እስከ ንጉሡ መጥመቂያ ድረስ በስፍራዋ ትኖራለች።


Follow us:

Advertisements


Advertisements