Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




መሳፍንት 18:8 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

8 ወደ ጾርዓና ወደ ኤሽታኦል እንደተመለሱ ወገኖቻቸው፥ “የሄዳችሁበት ጉዳይ እንዴት ሆነ?” በማለት ጠየቋቸው።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

8 ወደ ጾርዓና ወደ ኤሽታኦል እንደ ተመለሱ ወገኖቻቸው፣ “የሄዳችሁበት ጕዳይ እንዴት ሆነ?” በማለት ጠየቋቸው።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

8 አምስቱም ሰዎች ወደ ጾርዓና ወደ ኤሽታኦል በተመለሱ ጊዜ ወገኖቻቸው፦ “ምን ወሬ አላችሁ?” ብለው ጠየቁአቸው።

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

8 እነ​ዚ​ያም አም​ስቱ ሰዎች ወደ ወን​ድ​ሞ​ቻ​ቸው ወደ ሶራ​ሕና ወደ እስ​ታ​ሔል ተመ​ለሱ፤ ወን​ድ​ሞ​ቻ​ቸ​ው​ንም፥ “ምን አስ​ቀ​ም​ጦ​አ​ች​ኋል?” አሉ​አ​ቸው።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

8 ወደ ወንድሞቻቸውም ወደ ጾርዓና ወደ ኤሽታኦል ተመለሱ፥ ወንድሞቻቸውም፦ ምን ወሬ ይዛችኋል? አሉአቸው።

See the chapter Copy




መሳፍንት 18:8
7 Cross References  

ከዚያ በኋላም ከዳን ወገን ለጦርነት ዝግጁ የሆኑ ስድስት መቶ ሰዎች ከጾርዓና ከኤሽታኦል ተነሡ።


ስለዚህ ዳናውያን ምድሪቱን እንዲሰልሉና እንዲመረምሩ አምስት ኃያላን ሰዎች ከጾርዓና ከኤሽታኦል ከተሞች ወደዚያ ላኩ፤ እነዚህም ነገዶቻቸውን ሁሉ የሚወክሉ ነበሩ። የላኳቸውም ሰዎች፥ “ሂዱ፤ ምድሪቱን ሰልሉ” አሏቸው። መልእክተኞቹም ወደ ኰረብታማው የኤፍሬም አገር ገቡ፤ ወደሚያድሩበትም ወደ ሚካ ቤት መጡ።


ወንድሞቹና መላው የአባቱ ቤተሰብ ሬሳውን ለማምጣት ወደዚያ ወረዱ፤ አምጥተውም የአባቱ የማኑሄ መቃብር ባለበት በጾርዓና በኤሽታኦል መካከል ቀበሩት። ሳምሶን እስራኤልን ለሃያ ዓመት መሪ ሆኖ ነበር።


ማኑሄ የተባለ ከዳን ወገን የተወለደ አንድ የጾርዓ ሰው ነበረ፤ ሚስተ መካን ስለ ነበረች ልጅ አልወለደችም።


በቈላው ኤሽታኦል፥ ጾርዓ፥ አሽና፥


ስለዚህ አምስቱ ሰዎች ከዚያ ተነሥተው ወደ ላይሽ መጡ፤ ሲዶናውያን ያለ ስጋት በጸጥታ እንደሚኖሩ ሁሉ፥ በዚያም የሚኖረው ሕዝብ በሰላም እንደሚኖር አዩ። ምድሪቱ አንዳች የሚጐድላት ነገር ባለ መኖሩ ሕዝቡ ባለጸጋ ነበር። እንዲሁም ከሲዶናውያን ርቆ የሚኖር ሲሆን፥ ከማንኛውም ሕዝብ ጋር ግንኙነት አልነበረውም።


መልእክተኞቹም እንዲህ አሏቸው፤ “ምድሪቱ እጅግ መልካም መሆኗን አይተናል፤ እንግዲህ ተነሡ ሄደን እንዋጋቸው፤ ተነሡ እንጂ ዝም ትላላችሁን? ወደዚያው ሄዳችሁ ምድሪቱን ለመያዝ አታመንቱ!


Follow us:

Advertisements


Advertisements