Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




መሳፍንት 16:9 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

9 ሰዎች በጓዳ ውስጥ ተደብቀው ነበር፤ እርሷም፥ “ሳምሶን! ፍልስጥኤማውያን መጡብህ” አለችው፤ ሳምሶን ግን ፈትል እሳት ሲነካው እንደሚበጣጠስ ጠፍሮቹን በቀላሉ በጣጠሳቸው፤ ስለዚህ የብርታቱ ምስጢር ምን እንደሆነ ሊታወቅ አልቻለም።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

9 ሰዎች በጓዳ ውስጥ ተደብቀው ነበር፤ እርሷም፣ “ሳምሶን ፍልስጥኤማውያን መጡብህ” አለችው፤ ሳምሶን ግን ፈትል እሳት ሲነካው እንደሚበጣጠስ ጠፍሮቹን በቀላሉ በጣጠሳቸው። ስለዚህ የብርታቱ ምስጢር ምን እንደ ሆነ ሊታወቅ አልቻለም።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

9 በሌላ ክፍል ሆነው የሚጠባበቁ ወንዶች ስለ ነበሩ እርሷ “ሶምሶን! ፍልስጥኤማውያን መጡብህ!” ስትል ጮኸች፤ እርሱ ግን ፈትል እሳት ሲነካው እንደሚበጣጠስ ጠፍሮቹን በጣጠሳቸው፤ ስለዚህ አሁንም ብርታት የሚያገኝበትን ምሥጢር ገና አልደረሱበትም ነበር።

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

9 የሚ​ያ​ደ​ቡ​ትም ሰዎች በጓ​ዳዋ ውስጥ ተደ​ብ​ቀው ነበር። እር​ስ​ዋም፥ “ሶም​ሶን ሆይ! ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን መጡ​ብህ” አለ​ችው። እር​ሱም ፈትል እሳት በሸ​ተ​ተው ጊዜ እን​ዲ​በ​ጠስ ጠፍ​ሩን በጣ​ጠ​ሰው፤ ኀይ​ሉም በምን እንደ ሆነ አል​ታ​ወ​ቀም።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

9 በጓዳዋም ውስጥ ሰዎች ተደብቀው ነበር። እርስዋም፦ ሶምሶን ሆይ፥ ፍልስጥኤማውያን መጡብህ አለችው። እርሱም የተልባ እግር ፈትል እሳት በሸተተው ጊዜ እንዲበጠስ ጠፍሩን በጣጠሰው፥ ኃይሉም በምን እንደ ሆነ አልታወቀም።

See the chapter Copy




መሳፍንት 16:9
5 Cross References  

እንደሚሟሟ ቀንድ አውጣ፥ ፀሐይን እንዳላየ ጭንጋፍ ይሁኑ።


ሳምሶንም፥ “ማንም ባልደረቁ ሰባት እርጥብ ጠፍሮች ቢያስረኝ እንደ ማንኛውም ሰው ደካማ እሆናለሁ” አላት።


ከዚያም የፍልስጥኤማውያን ገዦች ያልደረቁ ሰባት እርጥብ ጠፍሮች አመጡላት፤ እርሷም አሰረችው።


ደሊላም ሳምሶንን፥ “አሞኝተኸኛል፤ ዋሽተኸኛል፤ እባክህ አሁንም አንተን እንዴት ማሰር እንደሚቻል ንገረኝ” አለችው።


ሳምሶን ሌሒ እንደደረሰም ፍልስጥኤማውያን እየጮኹ ወደ እርሱ መጡ፤ በዚህ ጊዜ የጌታ መንፈስ በሳምሶን ላይ በኃይል ወረደበት። እጆቹ የታሰሩበትም ገመድ እሳት ውስጥ እንደ ገባ የተልባ እግር ፈትል ሆኖ ከእጆቹ ላይ ወደቀ።


Follow us:

Advertisements


Advertisements