መሳፍንት 16:20 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)20 እርሷም፥ “ሳምሶን፤ ፍልስጥኤማውያን መጡብህ” አለችው። ሳምሶን ከእንቅልፉ ነቅቶ፥ “እንደ ወትሮው አደርጋለሁ” አለ፤ ነገር ግን ጌታ እንደ ተወው አላወቀም ነበር። See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም20 እርሷም፣ “ሳምሶን፤ ፍልስጥኤማውያን መጡብህ!” አለችው። ሳምሶን ከእንቅልፉ ነቅቶ፣ “እንደ ወትሮው አደርጋለሁ” አለ፤ ነገር ግን እግዚአብሔር እንደ ተወው አላወቀም ነበር። See the chapterአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም20 ከዚያም በኋላ “ሶምሶን! ፍልስጥኤማውያን መጡብህ!” አለችው፤ እርሱም ከእንቅልፉ ነቅቶ “እንደ ወትሮው በጣጥሼ እሄዳለሁ” ብሎ አሰበ፤ እግዚአብሔርም እንደ ተለየው አላወቀም ነበር፤ See the chapterየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)20 ደሊላም፥ “ሶምሶን ሆይ! ፍልስጥኤማውያን መጡብህ” አለችው። ከእንቅልፉም ነቅቶ፥ “እወጣለሁ፤ እንደ ወትሮውም ጊዜ አደርጋለሁ፤ አጠፋቸዋለሁም” አለ። ነገር ግን እግዚአብሔር ከእርሱ እንደ ተለየው አላወቀም። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)20 እርስዋም፦ ሶምሶን ሆይ፥ ፍልስጥኤማውያን መጡብህ አለችው። ከእንቅልፉም ነቅቶ፦ እወጣለሁ እንደ ወትሮውም ጊዜ አደርጋለሁ አለ። ነገር ግን እግዚአብሔር ከእርሱ እንደ ተለየው አላወቀም። See the chapter |