መሳፍንት 14:4 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)4 በዚያን ጊዜ በእስራኤል ላይ ገዦቹ ፍልስጥኤማውያን ስለ ነበሩ፥ ከፍልስጥአማውያን ጋር ጠብ እንዲፈጠር ጌታ ሆን ብሎ ያደረገው ነገር መሆኑን አባቱና እናቱ አላወቁም ነበር። See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም4 በዚያ ጊዜ በእስራኤል ላይ ገዦቹ ፍልስጥኤማውያን ስለ ነበሩ፣ ከፍልስጥኤማውያን ጋራ ጠብ እንዲፈጠር እግዚአብሔር ሆነ ብሎ ያደረገው ነገር መሆኑን አባቱና እናቱ አላወቁም ነበር። See the chapterአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም4 ሶምሶን ይህን እንዲያደርግ የሚመራው እግዚአብሔር እንደ ሆነ ወላጆቹ አላወቁም፤ በዚያም ጊዜ ፍልስጥኤማውያን እስራኤላውያንን ይገዙ ስለ ነበር፥ እግዚአብሔር ፍልስጥኤማውያንን ለመቃወም ምክንያት ይፈልግ ነበር። See the chapterየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)4 አባቱና እናቱም ነገሩ ከእግዚአብሔር እንደ ሆነ አላወቁም፤ እርሱ ከፍልስጥኤማውያን በቀልን ይመልስ ዘንድ ይፈልግ ነበርና። በዚያም ወራት ፍልስጥኤማውያን እስራኤልን ይገዙ ነበር። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)4 እግዚአብሔርም በፍልስጥኤማውያን ላይ ምክንያት ይፈልግ ነበርና ነገሩ ከእርሱ ሆነ፥ አባቱና እናቱ ግን አላወቁም። በዚያን ጊዜም ፍልስጥኤማውያን በእስራኤል ላይ ገዦች ነበሩ። See the chapter |