መሳፍንት 14:18 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)18 በሰባተኛው ቀን ፀሓይ ከመጥለቋ በፊት የከተማው ሰዎች፥ “ከማር የጣፈጠ ምን ተገኝቶ? ከአንበሳስ ወዲያ ብርቱ ከየት መጥቶ” አሉት። ሳምሶንም መልሶ፥ “በጊደሬ ባላረሳችሁ፥ እንቈቅልሼንም ባልፈታችሁ” አላቸው። See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም18 በሰባተኛው ቀን ፀሓይ ከመጥለቋ በፊት የከተማው ሰዎች፣ “ከማር የጣፈጠ ምን ተገኝቶ? ከአንበሳስ ወዲያ ብርቱ ከየት መጥቶ!” አሉት። ሳምሶንም መልሶ፣ “በጊደሬ ባላረሳችሁ፣ እንቈቅልሼንም ባልፈታችሁ” አላቸው። See the chapterአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም18 ስለዚህ በሰባተኛው ቀን ፀሐይ ከመጥለቋ በፊት፥ የከተማይቱ ሰዎች “ከማር የጣፈጠ፥ ከአንበሳስ የበረታ ምን አለ?” ሲሉ የእንቆቅልሹን ፍች ነገሩት። ሶምሶንም “በእኔ ጊደር ባታርሱ ኖሮ፥ መልሱን ማግኘት ባልቻላችሁም ነበር” አላቸው። See the chapterየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)18 በሰባተኛዪቱም ቀን ፀሐይ ሳትገባ የከተማዪቱ ሰዎች፥ “ከማር የሚጣፍጥ ምንድን ነው? ከአንበሳስ የሚበረታ ማን ነው?” አሉት። ሶምሶንም፥ “በጥጃዬ ባላረሳችሁ ኑሮ የእንቆቅልሼን ትርጓሜ ባላወቃችሁም ነበር” አላቸው። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)18 በሰባተኛውም ቀን ፀሐይ ሳትገባ የከተማይቱ ሰዎች፦ ከማር የሚጣፍጥ ምንድር ነው? ከአንበሳስ የሚበረታ ማን ነው? አሉት። እርሱም፦ በጥጃዬ ባላረሳችሁ የእንቈቅልሼን ትርጓሜ ባላወቃችሁ ነበር አላቸው። See the chapter |