መሳፍንት 12:9 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)9 እርሱም ሠላሳ ወንዶችና ሠላሳ ሴቶች ልጆች ነበሩት። ሴቶች ልጆቹንም ከጐሣው ውጭ ለሆኑ ሰዎች ዳራቸው፤ ጐሣው ውጭ የሆኑ ሠላሳ ልጃገረዶች አምጥቶ ከወንዶች ልጆቹ ጋር አጋባቸው። ኢብጻን በእስራኤል ላይ ሰባት ዓመት ፈራጅ ሆነ። See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም9 እርሱም ሠላሳ ወንዶችና ሠላሳ ሴቶች ልጆች ነበሩት። ሴቶች ልጆቹንም ከጐሣው ውጭ ለሆኑ ሰዎች ዳራቸው፤ ከጐሣው ውጭ የሆኑ ሠላሳ ልጃገረዶች አምጥቶ ከወንዶች ልጆቹ ጋራ አጋባቸው። ኢብጻን በእስራኤል ላይ ሰባት ዓመት ፈራጅ ሆነ። See the chapterአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም9 ኢብጻን ሠላሳ ወንዶችና ሠላሳ ሴቶች ልጆች ነበሩት፤ ሴቶች ልጆቹን ከጐሣው ውጪ ከሆኑ ወንዶች ጋር አጋባቸው፤ እንዲሁም ከጐሣው ውጪ የሆኑ ሴቶች ልጆችን አምጥቶ ከወንዶች ልጆቹ ጋር እንዲጋቡ አደረገ፤ ኢብጻን ሰባት ዓመት የእስራኤል መሪ ሆነ። See the chapterየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)9 ሠላሳ ወንዶች ልጆችና ሠላሳ ሴቶች ልጆችንም ወለደ፤ ሠላሳ ሴቶች ልጆቹንም ወደ ውጭ ሀገር ዳረ፤ ለወንዶች ልጆቹም ከውጭ ሀገር ሠላሳ ሴቶች ልጆችን አመጣ። እስራኤልንም ሰባት ዓመት ገዛ። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)9 ሠላሳም ወንዶች ልጆችና ሠላሳ ሴቶች ልጆች ነበሩት፥ ሠላሳ ሴቶች ልጆቹንም ወደ ውጭ አገር ዳረ፥ ለወንዶች ልጆቹም ከውጭ አገር ሴቶች ልጆችን አመጣ። በእስራኤልም ላይ ሰባት ዓመት ፈረደ። See the chapter |