መሳፍንት 12:5 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)5 ገለዓዳውያን ወደ ኤፍሬም የሚያሻግሩትን የዮርዳኖስን መሻገሪያዎች ያዙ፤ ታድያ አምልጦ የሚሸሽ አንድ ኤፍሬማዊ ለመሻገር በሚጠይቃቸው ጊዜ፥ የገለዓድ ሰዎች “አንተ ኤፍሬማዊ ነህ?” ብለው ይጠይቁታል፤ ያም ሰው፥ “አይደለሁም” ብሎ ከመለሰላቸው፥ See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም5 ገለዓዳውያን ወደ ኤፍሬም የሚያሻግሩትን የዮርዳኖስን መልካዎች ያዙ። ታዲያ አምልጦ የሚሸሽ አንድ ኤፍሬማዊ ለመሻገር በሚጠይቃቸው ጊዜ፣ የገለዓድ ሰዎች “አንተ ኤፍሬማዊ ነህ?” ብለው ይጠይቁታል፤ ያም ሰው፣ “አይደለሁም” ብሎ ከመለሰላቸው፣ See the chapterአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም5 የኤፍሬም ሰዎች እንዳያመልጡ ለማድረግ ገለዓዳውያን የዮርዳኖስን መሻገሪያ ቦታዎች ሁሉ ዘግተው ያዙ፤ ለማምለጥ የሚሞክር ማንኛውም የኤፍሬም ሰው ለመሻገር ፈቃድ ቢጠይቅ ገለዓዳውያን “አንተ የኤፍሬም ሰው ነህን?” ብለው ይጠይቁት ነበር፤ “አይደለሁም!” ካለ፥ See the chapterየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)5 የገለዓድ ሰዎችም ኤፍሬም በሚያልፍበት በዮርዳኖስ ማዶ ደረሱባቸው። ከዚህ በኋላ ከኤፍሬም ያመለጡት እንሻገር ባሉ ጊዜ የገለዓድ ሰዎች፥ “በውኑ እናንተ ከኤፍሬም ወገን ናችሁን?” ቢሉአቸው “አይደለንም” አሉ። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)5 ገለዓዳውያንም ኤፍሬም የሚያልፍበትን የዮርዳኖስን መሻገርያ ያዙባቸው፥ የሸሸም የኤፍሬም ሰው፦ ልለፍ ባለ ጊዜ፥ የገለዓድ ሰዎች፦ አንተ ኤፍሬማዊ ነህን? አሉት፥ እርሱም፦ አይደለሁም ቢል፥ See the chapter |