መሳፍንት 11:2 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)2 የገለዓድ ሚስትም ለገለዓድ ወንዶች ልጆች ወለደችለት፤ እነርሱም ባደጉ ጊዜ ዮፍታሔን፥ “ከሌላ ሴት ስለተወለድህ ከቤተሰባችን ምንም ዓይነት ውርስ አይገባህም” በማለት አሳደዱት። See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም2 እንደዚሁም የገለዓድ ሚስት ለገለዓድ ወንዶች ልጆች ወለደችለት፤ እነርሱም ባደጉ ጊዜ ዮፍታሔን፣ “ከሌላ ሴት ስለ ተወለድህ ከቤተ ሰባችን ምንም ዐይነት ውርስ አይገባህም” በማለት አሳደዱት። See the chapterአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም2 የእርሱ አባት ገለዓድ ቀደም ብሎ ያገባት ሚስቱ የወለደችለት ሌሎች ወንዶች ልጆች ነበሩት፤ እነርሱም ባደጉ ጊዜ ወንድማቸውን ዮፍታሔን “አንተ ከሌላ ሴት የተወለድክ ስለ ሆንክ ከአባታችን ርስት ምንም ነገር መውረስ አይገባህም” ብለው ከቤት እንዲባረር አደረጉት። See the chapterየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)2 የገለዓድም ሚስት ወንዶች ልጆችን ወለደችለት፤ ልጆችዋም ባደጉ ጊዜ ዮፍታሔን፥ “የሌላ ሴት ልጅ ነህና በአባታችን ቤት አትወርስም” ብለው አስወጡት። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)2 የገለዓድም ሚስት ወንዶች ልጆችን ወለደችለት፥ ልጆችዋም ባደጉ ጊዜ ዮፍታሔን፦ የልዩ ሴት ልጅ ነህና በአባታችን ቤት አትወርስም ብለው አሳደዱት። See the chapter |