Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




መሳፍንት 11:18 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

18 “ቀጥሎም የኤዶምንና የሞዓብን ምድር በመዞር፥ በምድረ በዳው ተጉዞ ከሞዓብ በስተ ምሥራቅ በኩል በማለፍ ከአርኖን ማዶ ሰፈረ፤ የሞዓብም ድንበር አርኖን ስለ ነበር ወደ ሞዓብ ክልል አልገባም።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

18 “ቀጥሎም የኤዶምንና የሞዓብን ምድር በመዞር፣ በምድረ በዳው ተጕዞ ከሞዓብ በስተምሥራቅ በኩል በማለፍ ከአርኖን ማዶ ሰፈረ፤ የሞዓብም ድንበር አርኖን ስለ ነበር ወደ ሞዓብ ክልል አልገባም።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

18 በረሓውንም በማቋረጥ ጒዞ ቀጥለው የኤዶምንና የሞአብን ምድር በመዞር ከሞአብ በስተምሥራቅና ከአርኖን ወንዝ ባሻገር ወዳለው ስፍራ መጥተው ሰፈሩ፤ ነገር ግን የሞአብ ወሰን ስለ ነበር የአርኖንን ወንዝ አልተሻገሩም፤

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

18 እስ​ራ​ኤ​ልም በቃ​ዴስ ተቀ​መጠ። በም​ድረ በዳም በኩል አለፈ፤ የኤ​ዶ​ም​ያ​ስ​ንና የሞ​ዓ​ብ​ንም ምድር ዞሩ፤ ከሞ​ዓብ ምድ​ርም በም​ሥ​ራቅ በኩል መጡ፤ በአ​ር​ኖ​ንም ማዶ ሰፈሩ፤ አር​ኖ​ንም የሞ​ዓብ ድን​በር ነበ​ረና ወደ ሞዓብ ድን​በር አል​ገ​ቡም።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

18 እስራኤልም በቃዴስ ተቀመጠ። በምድረ በዳም በኩል ሄዱ፥ የኤዶምያስንና የሞዓብንም ምድር ዞሩ፥ ከሞዓብ ምድርም በምሥራቅ በኩል መጡ በአርኖንም ማዶ ሰፈሩ፥ አርኖንም የሞዓብ ድንበር ነበረና የሞዓብን ድንበር አላለፉም።

See the chapter Copy




መሳፍንት 11:18
8 Cross References  

ባላቅም በለዓም እንደመጣ በሰማ ጊዜ በአርኖን ድንበር በድንበሩም ጨረሻ ወዳለችው ወደ ሞዓብ ከተማ ሊገናኘው ወጣ።


ከቃዴስም ተጓዙ፤ የእስራኤልም ልጆች ማኅበር ሁሉ ወደ ሖር ተራራ መጡ።


ጌታም አለኝ፦ ‘እኔ ዔርን ለሎጥ ልጆች ርስት አድርጌ ስለ ሰጠሁ፥ ከእነርሱ ምድር ምንም አልሰጣችሁምና ሞዓባውያንን አትጣላ በውጊያም አትጋፈጣቸው።’”


‘አንተ ዛሬ የሞዓብን ዳርቻ ዔርን ታልፋለህ፤


“ደግሞም አለ፦ ‘ተነሥታችሁ ሂዱ፥ የአርኖንንም ሸለቆ ተሻገሩ፥ እነሆ፥ አሞራዊውን የሐሴቦንን ንጉሥ ሴዎንን ምድሩንም በእጅህ አሳልፌ ሰጥቼሃለሁ፤ እርሷን በመውረስ ጀምር፥ ከእርሱም ጋር ተዋጋ።


Follow us:

Advertisements


Advertisements