መሳፍንት 1:14 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)14 እርሷም ወደ ዖትኒኤል በመጣች ጊዜ፥ ከአባቷ የእርሻ መሬት እንዲጠይቅ መከረችው፤ ካሌብም እርሷ ከአህያዋ ላይ እንደወረደች “ምን እንዳደርግልሽ ትፈልጊያለሽ?” ሲል ጠየቃት። See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም14 እርሷም ወደ ጎቶንያል በመጣች ጊዜ፣ አባቷ የዕርሻ መሬት እንዲሰጠው ይለምነው ዘንድ አጥብቃ ነገረችው፤ ካሌብም እርሷ ከአህያዋ ላይ እንደ ወረደች “ምን እንዳደርግልሽ ትፈልጊያለሽ?” ሲል ጠየቃት። See the chapterአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም14 በጋብቻቸውም ቀን ዖትኒኤል ዓክሳን “አባትሽ የእርሻ መሬት እንዲሰጥሽ ጠይቂ” አላት፤ እርስዋም ካሌብን ስታይ ከበቅሎዋ ላይ ወረደች፤ ካሌብም “ምን እንድሰጥሽ ትፈልጊአለሽ” ብሎ ጠየቃት። See the chapterየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)14 እርስዋም ወደ እርሱ በመጣች ጊዜ የእርሻ ቦታ ይሰጣት ዘንድ አባቷን እንድትለምነው ጎቶንያል መከራት። እርስዋም በአህያዋ ላይ ሆና አንጐራጐረች፤ “ወደ ደቡብ ሰድደኸኛል” ብላም ጮኸች። ካሌብም፥ “ምን ሆነሻል?” አላት። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)14 እርስዋም ወደ እርሱ በመጣች ጊዜ ከአባትዋ እርሻ እንዲለምን መከረችው። እርስዋም ከአህያዋ ወረደች፥ ካሌብም፦ ምን ፈለግሽ? አላት። See the chapter |