መሳፍንት 1:10 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)10 የይሁዳ ሰዎች በኬብሮን በሚኖሩ ከነዓናውያን ላይ ዘመቱ፤ ኬብሮን ቀደም ሲል ቂርያት-አርባዕ ተብላ ትጠራ ነበር፤ እነርሱም ሼሻይን፥ አሒማንንና ታልማይኖችን ድል አደረጉ። See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም10 ቀደም ሲል ቂርያት አርባቅ ተብላ በምትጠራው በኬብሮን በሚኖሩት ከነዓናውያን ላይ ዘመቱ፤ ሴሲንን፣ አኪመንንና ተላሚንን ድል አደረጉ። See the chapterአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም10 የይሁዳ ሰዎች በኬብሮን በሚኖሩ ከነዓናውያን ላይ ዘመቱ፤ ኬብሮን ቀድሞ ኪርያት አርባዕ ትባል ነበር፤ እነርሱም የሼሻይን፥ የአሒማንንና የታልማይን ጐሣዎች አሸነፉ። See the chapterየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)10 ይሁዳም በኬብሮን ወደሚኖሩ ከነዓናውያን ሄደ። የኬብሮንም ሰዎች ወጥተው ተቀበሉት፤ የኬብሮንም ስም አስቀድሞ ቂርያታርቦቅሴፌር ነበረ። የኤናቅንም ትውልድ ሴሲንና አኪማምን፥ ተለሜንንም ገደሉአቸው። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)10 ይሁዳም በኬብሮን የሚኖሩትን ከነዓናውያንን ሊወጋ ሄደ። የኬብሮንም ስም አስቀድሞ ቂርያትአርባቅ ነበረ። ሴሲንና አኪመንን ተላሚንም ገደሉ። See the chapter |