Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ኢያሱ 9:2 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

2 ኢያሱንና እስራኤልን ሊወጉ አንድ ሆነው ተሰበሰቡ።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

2 ኢያሱንና እስራኤልን ለመውጋት በአንድነት መጡ።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

2 ኀይላቸውን በአንድነት አስተባብረው በኢያሱና በእስራኤላውያን ላይ ለመዝመት መጡ።

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

2 ኢያ​ሱ​ንና እስ​ራ​ኤ​ልን ሁሉ ሊወጉ አንድ ሆነው ተሰ​በ​ሰቡ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

2 ኢያሱንና እስራኤልን ሊወጉ አንድ ሆነው ተሰበሰቡ።

See the chapter Copy




ኢያሱ 9:2
15 Cross References  

የአጋንንት መናፍስት ናቸውና፥ ምልክት እያደረጉ፥ በታላቁና ሁሉን በሚገዛው በእግዚአብሔር ቀን ለሚሆነው ጦርነት እንዲያስከትቱአቸው ወደ ዓለም ሁሉ ነገሥታት ይወጣሉ።


እነሆ፥ ጥቃት ቢደርስብሽ፥ ከእኔ ዘንድ ግን አይሆንም፤ በአንቺም ላይ የሚነሡ ሁሉ ከአንቺ የተነሣ ይወድቃሉ።


“እነዚህ ሰዎች፤ ‘አድማ’ ብለው የሚጠሩትን፤ ማንኛውንም ነገር፤ ‘አድማ’ አትበሉ፤ እነርሱ የሚፈሩትን አትፍሩ፤ አትሸበሩለትም።


ክፉ ሰው በእርግጠኛነት ሳይቀጣ አይቀርም፥ የጻድቃን ዘር ግን ይድናል።


አምስቱም የአሞራውያን ነገሥታት፥ የኢየሩሳሌም ንጉሥ፥ የኬብሮን ንጉሥ፥ የየርሙት ንጉሥ፥ የለኪሶ ንጉሥ፥ የዔግሎም ንጉሥ፥ እነርሱና ከሠራዊቶቻቸው ሁሉ ጋር ተሰብስበው ወጡ፥ በገባዖንም ዙርያ ሰፈሩ በእርሷም ላይ ጦርነት አደረጉ።


እንዲህም ሆነ፤ የአሦር ንጉሥ ኢያቢስ ይህን በሰማ ጊዜ ወደ ማዶን ንጉሥ ወደ ዮባብ፥ ወደ ሺምሮንም ንጉሥ፥ ወደ አክሻፍም ንጉሥ፥


እነዚህም ነገሥታት ሁሉ ኃይላቸውን አስተባብረው እስራኤልን ለመውጋት መጡ፤ በማሮንም ውኃ አጠገብ በአንድ ላይ ሰፈሩ።


ዮርዳኖስንም ተሻገራችሁ፥ ወደ ኢያሪኮም መጣችሁ፤ የኢያሪኮም ሰዎች፥ አሞራዊው፥ ፌርዛዊው፥ ከነዓናዊው፥ ኬጢያዊው፥ ጌርጌሳዊው፥ ኤዊያዊው፥ ኢያቡሳዊው ተዋጉአችሁ፤ አሳልፌም በእጃችሁ ሰጠኋቸው።


Follow us:

Advertisements


Advertisements