ኢያሱ 8:11 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)11 ከእርሱም ጋር የነበሩ ተዋጊዎች ሁሉ ወጥተው በመጓዝ ወደ ከተማይቱ ቀረቡ፥ በጋይም በሰሜን በኩል ሰፈሩ፤ በእነርሱና በጋይም መካከል ሸለቆ ነበረ። See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም11 ከርሱ ጋራ የነበሩትም ተዋጊዎች በሙሉ ወጥተው ወደ ከተማዪቱ በመጠጋት ከፊት ለፊቷ ደረሱ፤ ከዚያም ከጋይ በስተሰሜን መካከል ካለው ሸለቆ ማዶ ሰፈሩ። See the chapterአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም11 ከእርሱም ጋር የነበረው ሠራዊት ወደ ፊት ቀድሞ በመጓዝ ወደ ከተማይቱ ቀረበ፤ በስተሰሜንም በኩል በእርሱና በዐይ መካከል ካለው ሸለቆ ማዶ ሰፈረ። See the chapterየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)11 ከእርሱም ጋር የነበሩ ተዋጊዎች ሕዝብ ሁሉ ወጥተው ቀረቡ፤ ወደ ከተማዪቱም ፊት ደረሱ፤ በጋይም በምሥራቅ በኩል ሰፈሩ፤ በእነርሱና በጋይም መካከል ሸለቆ ነበረ። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)11 ከእርሱም ጋር የነበሩ ሰልፈኞች ሁሉ ወጥተው ቀረቡ፥ ወደ ከተማይቱም ፊት ደረሱ፥ በጋይም በሰሜን በኩል ሰፈሩ፥ በእነርሱና በጋይም መካከል ሸለቆ ነበረ። See the chapter |