ኢያሱ 24:7 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)7 ወደ ጌታም በጮኹ ጊዜ በእናንተና በግብፃውያን መካከል ጨለማ አደረገ፥ ባሕሩንም መለሰባቸው፥ አሰጠማቸውም፤ ዐይኖቻችሁም በግብጽ ያደረግሁትን አዩ፤ በምድረ በዳም ብዙ ጊዜ ተቀመጣችሁ። See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም7 እነርሱ ግን ወደ እግዚአብሔር ጮኹ፤ እርሱም በእናንተና በግብጻውያን መካከል ጨለማ እንዲሆን አደረገ። ባሕሩን በላያቸው አመጣ፤ አሰጠማቸውም። በግብጻውያን ላይ ያደረግሁትንም ራሳችሁ በዐይናችሁ አያችሁ፤ በምድረ በዳም ብዙ ጊዜ ኖራችሁ። See the chapterአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም7 እረዳቸው ዘንድ ወደ እኔ ጮኹ፤ እኔም በእነርሱና በግብጻውያን መካከል ጨለማ እንዲሆን አደረግሁ። ባሕሩም እንዲከነበልባቸው አድርጌ ግብጻውያንን አሰጠምሁ፤ በግብጻውያን ላይ ምን እንዳደረግሁ በዐይኖቻችሁ አይታችኋል፤ ከዚያም በኋላ እናንተ ለብዙ ጊዜ በበረሓ ኖራችሁ። See the chapterየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)7 ወደ እግዚአብሔርም በጮሃችሁ ጊዜ በእናንተና በግብፃውያን መካከል ደመናንና ጭጋግን አደረግሁ፤ ባሕሩንም መለስሁባቸው፤ አሰጠማቸውም፤ ዐይኖቻችሁም በግብፅ ያደረግሁትን አዩ፤ በምድረ በዳም ብዙ ጊዜ ተቀመጣችሁ። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)7 ወደ እግዚአብሔርም በጮኹ ጊዜ በእናንተና በግብፃውያን መካከል ጨለማ አደረገ፥ ባሕሩንም መለሰባቸው፥ አሰጠማቸውም፥ ዓይኖቻችሁም በግብፅ ያደረግሁትን አዩ፥ በምድረ በዳም ብዙ ጊዜ ተቀመጣችሁ። See the chapter |