ኢያሱ 22:16 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)16 “የጌታ ማኅበር ሁሉ የሚለው ይህ ነው፦ ‘ዛሬ ጌታን ከመከተል በመመለሳችሁ፥ መሠዊያም ሠርታችሁ ዛሬ በጌታ ላይ በማመፃችሁ ይህ በእስራኤል አምላክ ላይ ያደረጋችሁት አለመታመን ምንድነው? See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም16 “መላው የእግዚአብሔር ጉባኤ እንዲህ ይላል፤ ‘በእስራኤል አምላክ ላይ እንዲህ ያለ ክሕደት የፈጸማችሁት ለምንድን ነው? እግዚአብሔርን ከመከተልስ እንዴት ወደ ኋላ ትላላችሁ? እንዴትስ ዛሬ በእግዚአብሔር ላይ ዐምፃችሁ ለራሳችሁ መሠዊያ ትሠራላችሁ? See the chapterአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም16 “የእግዚአብሔር ሕዝብ የሚለው እንዲህ ነው፦ ‘በእስራኤል አምላክ ላይ ያላችሁን እምነት እንዴት ታጓድላላችሁ? ለራሳችሁ መሠዊያ በመሥራት ከእግዚአብሔር ርቃችኋል፤ በእርሱም ላይ ዐምፃችኋል፤ See the chapterየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)16 የእግዚአብሔር ማኅበር ሁሉ የሚለው ይህ ነው፥ “ዛሬ እግዚአብሔርን መከተልን ትተዉ ዘንድ፥ መሠዊያም ትሠሩ ዘንድ፥ እግዚአብሔርንም ዛሬ ትክዱት ዘንድ ይህ በእስራኤል አምላክ ፊት ያደረጋችሁት ኀጢአት ምንድን ነው? See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)16 እንዲህም ብለው ተናገሩአቸው፦ የእግዚአብሔር ማኅበር ሁሉ የሚለው ይህ ነው፦ ይህ በእስራኤል አምላክ ላይ ያደረጋችሁት ኃጢአት ምንድር ነው? ዛሬ እግዚአብሔርን ከመከተል ተመልሳችኋል፥ ዛሬም መሠዊያ በመሥራታችሁ በእግዚአብሔር ላይ ዐምፃችኋል። See the chapter |