Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ኢያሱ 18:11 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

11 የብንያምም ልጆች ነገድ ዕጣ በየወገኖቻቸው ወጣ፤ የዕጣቸውም ግዛት በይሁዳ ልጆችና በዮሴፍ ልጆች መካከል ወጣ።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

11 ለብንያም ነገድ የሆነው የመጀመሪያው ዕጣ በየጐሣ በየጐሣው ወጣ። በዕጣ የደረሳቸውም ምድር የሚገኘው በይሁዳና በዮሴፍ ነገዶች ርስት መካከል ሲሆን እንደሚከተለው ነው፤

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

11 የብንያም ነገድ የርስት ድርሻ በየወገናቸው ወጣ፤ ለእነርሱም የተመደበላቸው ርስት የሚገኘው በይሁዳና በዮሴፍ ነገዶች መካከል ነበር፤

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

11 የብ​ን​ያ​ምም ነገድ ዕጣ በየ​ወ​ገ​ኖ​ቻ​ቸው በቅ​ድ​ሚያ ወጣ፤ የዕ​ጣ​ቸ​ውም ዳርቻ በይ​ሁዳ ልጆ​ችና በዮ​ሴፍ ልጆች መካ​ከል ወጣ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

11 የብንያምም ልጆች ነገድ ዕጣ በየወገኖቻቸው ወጣ፥ የዕጣቸውም ዳርቻ በይሁዳ ልጆችና በዮሴፍ ልጆች መካከል ወጣ።

See the chapter Copy




ኢያሱ 18:11
9 Cross References  

“አምላክህ ጌታ እንድትኖርባቸው ከሚሰጥህ ከተሞች በአንዲቱ ውስጥ እንዲህ ሲባል ብትሰማ፥


ኢያሱም በጌታ ፊት በሴሎ ዕጣ ጣለላቸው፤ በዚያም ኢያሱ ለእስራኤል ልጆች እንደየድርሻቸው ምድሩን ከፈለ።


በሰሜን በኩል ድንበራቸው ከዮርዳኖስ ጀመረ፤ ድንበሩም ወደ ኢያሪኮ ወደ ሰሜን ወገን ወጣ፥ ከዚያም በተራራማው አገር በኩል ወደ ምዕራብ ወጣ፥ መጨረሻውም በቤትአዌን ምድረ በዳ ነበረ።


የራሔል ልጆች፥ ዮሴፍና ብንያም ናቸው።


እርሱንም በገለዓድ ላይ፥ በአሴር፥ በኢይዝራኤል፥ በኤፍሬምና በብንያም እንዲሁም በእስራኤል ሁሉ አነገሠው።


ለቀሩትም ነገዶች እንዲህ ይሆናል፤ ከምሥራቅ ጀምሮ እስከ ምዕራብ ድረስ ለብንያም አንድ የዕጣ ክፍል ይሆናል።


Follow us:

Advertisements


Advertisements