Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ኢያሱ 16:9 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

9 ይኸውም በምናሴ ልጆች ርስት መካከል ለኤፍሬም ልጆች ከተለዩ ከተሞች ጋር፥ እነዚህም ከተሞች ሁሉ ከመንደሮቻቸው ጋር ርስታቸው ነበሩ።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

9 ይህም በምናሴ ነገድ ርስት ውስጥ ለኤፍሬም ዘሮች የተመደቡትን ከተሞች በሙሉና መንደሮቻቸውን የሚያጠቃልል ነው።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

9 እርሱም በምናሴ ርስት ክልል ውስጥ ያሉትንና ለኤፍሬማውያን የተሰጡትን ከተሞችና መንደሮችንም ይጨምራል፤

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

9 ይኸ​ውም በም​ናሴ ልጆች ርስት መካ​ከል ለኤ​ፍ​ሬም ልጆች ከተ​ለዩ ከተ​ሞች ጋር፥ ከተ​ሞች ሁሉ ከመ​ን​ደ​ሮ​ቻ​ቸው ጋር ነው።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

9 ይኸውም በምናሴ ልጆች ርስት መካከል ለኤፍሬም ልጆች ከተለዩ ከተሞች ጋር፥ ከተሞች ሁሉ ከመንደሮቻቸው ጋር፥ ነው።

See the chapter Copy




ኢያሱ 16:9
6 Cross References  

ድንበሩም ወደ ቃና ወንዝ ወረደ፤ በምናሴም ከተሞች መካከል ከወንዙ በደቡብ በኩል የሚገኙት እነዚህ ከተሞች ለኤፍሬም ሆኑ፤ የምናሴም ድንበር በወንዙ በኩል በሰሜን ወገን ነበረ፥ መጨረሻውም በባሕሩ አጠገብ ነበረ።


ድንበሩም ከታጱዋ ወደ ምዕራብ እስከ ቃና ወንዝ ድረስ አለፈ፥ መጨረሻውም በባሕሩ አጠገብ ነበረ። የኤፍሬም ልጆች ነገድ ርስት በየወገኖቻቸው ይህ ነበረ።


በጌዝርም የተቀመጡትን ከነዓናውያንን አላሳደዱአቸውም፥ እስከ ዛሬም ድረስ ከነዓናውያን በኤፍሬም መካከል ተቀምጠዋል፤ እነርሱም የጉልበት ሥራ የሚሠሩ ባሮች ሆነዋል።


እርሱንም በገለዓድ ላይ፥ በአሴር፥ በኢይዝራኤል፥ በኤፍሬምና በብንያም እንዲሁም በእስራኤል ሁሉ አነገሠው።


ግዛታቸውና ማደሪያቸው ቤቴልና መንደሮችዋ፥ በምሥራቅም በኩል ነዓራን፥ በምዕራብም በኩል ጌዝርና መንደሮችዋ፥ ሴኬምና መንደሮችዋ ጋዛና መንደሮችዋ ነበሩ፤


ከምናሴ ድንበር ቀጥሎ ከምሥራቅ ጀምሮ እስከ ምዕራብ ድረስ ኤፍሬም አንድ ድርሻ ይኖረዋል።


Follow us:

Advertisements


Advertisements