Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ኢያሱ 16:3 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

3 ወደ ምዕራብም እስከ የፍሌጣውያን ድንበር እስከ ታችኛው ቤትሖሮን ድንበር እስከ ጌዝር ድረስ ወረደ፥ መጨረሻውም በባሕሩ አጠገብ ነበረ።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

3 በዚያም በምዕራብ በኩል ቍልቍል ወደ የፍሌጣውያን ግዛት እስከ ታችኛው ቤትሖሮን ምድር ይወርድና ወደ ጌዝር ዘልቆ ባሕሩ ላይ ይቆማል።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

3 ከዚያም በምዕራብ በኩል ወደሚገኙት ወደ ያፍሌጣውያን ይዞታ በመዝለቅ እስከ ታችኛው ቤትሖሮን ይደርሳል፤ ከዚያም ወደ ጌዜር ያልፍና መጨረሻው የሜድትራኒያን ባሕር ይሆናል።

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

3 ወደ ምዕ​ራ​ብም እስከ የፍ​ሌ​ጣ​ው​ያን ዳርቻ እስከ ታች​ኛው ቤቶ​ሮን ዳርቻ ድረስ ይወ​ር​ዳል፤ መው​ጫ​ውም በባ​ሕሩ አጠ​ገብ ነበረ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

3 ወደ ምዕራብም እስከ የፍሌጣውያን ዳርቻ እስከ ታችኛው ቤትሖሮን ዳርቻ እስከ ጌዝር ድረስ ወረደ፥ መውጫውም በባሕሩ አጠገብ ነበረ።

See the chapter Copy




ኢያሱ 16:3
9 Cross References  

ደግሞም ቅጥርና መዝጊያ መቀርቀሪያም የነበራቸውን የተመሸጉትን ከተሞች ላይኛውን ቤት-ሖሮን ታችኛውንም ቤት-ሖሮን ሠራ።


ድንበሩም ከዚያ በደቡብ በኩል በሎዛ አቅጣጫ ቤቴል ወደምትባል ወደ ሎዛ ወገን አለፈ፤ ድንበሩም በታችኛው ቤትሖሮን በደቡብ በኩል ባለው ተራራ ወደ አጣሮትአዳር ወረደ።


በዚያን ጊዜም የጌዝር ንጉሥ ሆራም ለኪሶን ለመርዳት ወጣ፤ ኢያሱም አንድም እንኳ ሳይቀር እርሱንና ሕዝቡን መታ።


ግዛታቸውና ማደሪያቸው ቤቴልና መንደሮችዋ፥ በምሥራቅም በኩል ነዓራን፥ በምዕራብም በኩል ጌዝርና መንደሮችዋ፥ ሴኬምና መንደሮችዋ ጋዛና መንደሮችዋ ነበሩ፤


ሴት ልጁም ታችኛውንና ላይኛውን ቤት-ሖሮንንና ኡዜን-ሼራን የሠራች ሲኦራ ነበረች።


“ለምዕራብም ድንበር ታላቁ ባሕርና ዳርቻው ድንበራችሁ ይሆናል፤ ይህ የምዕራብ ድንበራችሁ ይሆናል።


ሌላው ምድብ ወደ ቤትሖሮን፥ ሌላው ምድብ ደግሞ ከጸቦዒም ሸለቆና ከምድረ በዳው ፊት ለፊት ወደሚገኘው ድንበር አለፈ።


ከዚህም በኋላ በጌዝር ላይ ከፍልስጥኤማውያን ጋር ጦርነት ተደረገ፤ ኩሳታዊውም ሴቦካይ ከራፋይም ወገን የነበረውን ሲፋይን ገደለ። ፍልስጥኤማውያንም ተሸነፉ።


Follow us:

Advertisements


Advertisements