Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ኢያሱ 13:26 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

26 ከሐሴቦን ጀምሮ እስከ ራማት ምጽጴ፥ እስከ ብጦኒም ድረስ፥ ከመሃናይም ጀምሮ እስከ ዳቤር ዳርቻ ድረስ፥

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

26 ከሐሴቦን እስከ ራማት ምጽጳና ከዚያም እስከ ብጦኒም፣ ከመሃናይም እስከ ደቤር ግዛት ያለውን፣

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

26 የምድራቸውም ስፋት ከሐሴቦን ተነሥቶ እስከ ራማት ምጽጳና እስከ ቤጦኒም እንዲሁም ከማሕናይም ተነሥቶ እስከ ሎዴባር ድንበር ይደርሳል፤

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

26 ከሐ​ሴ​ቦን ጀምሮ እስከ አራ​ቦት መሴፋ፥ እስከ ቦጣ​ኒም ድረስ፥ ከማ​ኦን ጀምሮ እስከ ዴቦን ዳርቻ ድረስ፥

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

26 ከሐሴቦን ጀምሮ እስከ ራማት ምጽጴ፥ እስከ ብጦኒም ድረስ፥ ከመሃናይም ጀምሮ እስከ ዳቤር ዳርቻ ድረስ፥

See the chapter Copy




ኢያሱ 13:26
14 Cross References  

ዳዊት ማሕናይም ሲደርስ፥ ከአሞናውያን ከተማ ከራባ የመጣው፥ የናዖስ ልጅ ሾቢ፥ ከሎዶባር የመጣው የዓሚኤል ልጅ ማኪርና ከሮግሊም የመጣው ገለዓዳዊው ቤርዜሊ


በዚህ ጊዜ የሳኦል ሠራዊት አዛዥ የኔር ልጅ አበኔር፥ የሳኦልን ልጅ ኢያቡስቴን ወስዶ ወደ ማሕናይም አሻገረው፤


አክዓብ ባለሟሎቹ የሆኑትን ባለ ሥልጣኖች “በገለዓድ የምትገኘውን ራሞትን ከሶርያ ንጉሥ ለማስመለስ ምንም ዓይነት እርምጃ ያልወሰድነው ስለምንድን ነው? ራሞት እኮ የእኛ ይዞታ ናት!” አላቸው።


ከዚያም የጌታ መንፈስ በዮፍታሔ ላይ ወረደ፤ ተነሥቶም ገለዓድንና ምናሴን አቋርጦ ሄደ፤ ገለዓድ ባለችው በምጽጳ በኩል አድርጎም በአሞናውያን ላይ ዘመተባቸው።


ስለዚህ ዮፍታሔ ከገለዓድ አለቆች ጋር ሄደ፤ ሕዝቡም በላያቸው ላይ አለቃና አዛዥ አደረጉት፤ ዮፍታሔም የተናገረውን ቃል ሁሉ ምጽጳ ላይ በጌታ ፊት ደገመው።


አሞናውያን ለጦርነት ዝግጁ ሆነው በገለዓድ በሰፈሩ ጊዜ፥ እስራኤላውያንም እንደዚሁ ተሰብስበው በምጽጳ ሰፈሩ።


ከጋድም ነገድ ለነፍሰ ገዳይ መማፀኛ ከተማ የሆነችውን በገለዓድ ውስጥ ራሞትንና መሰማሪያዋን፥ መሃናይምንና መሰማሪያዋን፥


በዮርዳኖስም ማዶ ከኢያሪኮ ወደ ምሥራቅ ከሮቤል ነገድ በምድረ በዳው በደልዳላው ስፍራ ቦሶርን፥ ከጋድም ነገድ በገለዓድ ራሞትን፥ ከምናሴም ነገድ በባሳን ጎላንን ለዩ።


ደግሞም “ምጽጳ”፥ “እኛ አንዳችን ከሌላው በተለያየን ጊዜ ጌታ በእኔና በአንተ መካከል ሆኖ ይጠብቅ” ብሏልና።


ግዛታቸውም ኢያዜርና የገለዓድ ከተሞች ሁሉ፥ የአሞንም ልጆች ምድር እኩሌታ በረባት ፊት ለፊት እስካለችው እስከ አሮዔር ድረስ፥


በሸለቆውም ቤትሀራም፥ ቤትኒምራ፥ ሱኮት፥ ጻፎን፥ የተቀረውም የሐሴቦን ንጉሥ የሴዎን መንግሥት ነበረ። ድንበሩም ዮርዳኖስና በምሥራቅ በኩል ባለው በዮርዳኖስ ማዶ የኪኔሬት ባሕር ወዲያኛው ዳርቻ ነበር።


አሒናዳብ የተባለው የዒዶ ልጅ፦ የማሕናይም ክፍለ ሀገር ገዢ።


Follow us:

Advertisements


Advertisements