ኢያሱ 13:14 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)14 ለሌዊ ነገድ ግን ርስት አልሰጠም፤ እርሱ እንደ ተናገራቸው እንዲሁ ለእስራኤል አምላክ ለጌታ በእሳት የሚቀርበው መሥዋዕት ርስታቸው ነው። See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም14 ለሌዊ ነገድ ግን ርስት አልሰጠም፤ ለእስራኤል አምላክ ለእግዚአብሔር በእሳት የሚቀርበው ቍርባን በተሰጣቸው ተስፋ መሠረት ርስታቸው ነውና። See the chapterአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም14 ሙሴ ለሌዊ ነገድ የርስት ድርሻ አልሰጠም፤ እግዚአብሔር ሙሴን ባዘዘው መሠረት ለእስራኤል አምላክ ለእግዚአብሔር በመሠዊያ ላይ የሚቃጠል መሥዋዕት ሆኖ ከሚቀርበው መባ የሚያገኙት ድርሻ እንደ ርስት ሆኖ ተመድቦላቸዋል። See the chapterየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)14 ለሌዊ ነገድ ግን ርስት አልተሰጠም፤ እግዚአብሔር እንደ ተናገራቸው የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ርስታቸው ነውና፥ በኢያሪኮ በኩል በዮርዳኖስ ማዶ በሞዓብ ሜዳ ሙሴ ለእስራኤል ልጆች እንዳካፈላቸው እንዲሁ ተካፈሉ። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)14 ለሌዊ ነገድ ግን ርስት አልሰጠም፥ ለእስራኤል አምላክ ለእግዚአብሔር የቀረበው በእሳት የተደረገ መሥዋዕት ርስታቸው ነው፥ እርሱ እንደ ተናገራቸው። See the chapter |