Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ኢያሱ 10:41 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

41 ኢያሱም ከቃዴስ በርኔ እስከ ጋዛ ድረስ የጎሶምንም ምድር ሁሉ እስከ ገባዖን ድረስ መታ።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

41 ኢያሱም ከቃዴስ በርኔ እስከ ጋዛ እንዲሁም የጎሶምን ምድር ሁሉ እስከ ገባዖን ድረስ በሙሉ ያዘ።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

41 ኢያሱም ከቃዴስ በርኔ እስከ ጋዛ የጎሼንን አካባቢ ሁሉ ጨምሮ፥ እስከ ገባዖን ድረስ ወግቶ ድል አደረገ።

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

41 ኢያ​ሱም ከቃ​ዴስ በርኔ እስከ ጋዛ ድረስ፥ የጎ​ሶ​ም​ንም ምድር ሁሉ እስከ ገባ​ዖን ድረስ መታ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

41 ኢያሱም ከቃዴስ በርኔ እስከ ጋዛ ድረስ የጎሶምንም ምድር ሁሉ እስከ ገባዖን ድረስ መታ።

See the chapter Copy




ኢያሱ 10:41
19 Cross References  

ኢያሱም ያን ምድር ሁሉ፥ ተራራማውን፥ ደቡቡንም ሁሉ፥ የጎሶምንም ምድር ሁሉ፥ ቈላውንም፥ ዓረባንም፥ የእስራኤልንም ተራራማውንና ቈላውን ያዘ፥


ጎሶም፥ ሖሎን፥ ጊሎ፤ ዐሥራ አንድ ከተሞችና መንደሮቻቸው።


ጌታም፥ ‘ውጡ የሰጠኋችሁንም ምድር ውረሱ’ ብሎ ከቃዴስ በርኔ በላካችሁ ጊዜ፥ በጌታ በአምላካችሁ ቃል ላይ ዐመፃችሁ፥ በእርሱም አላመናችሁም፥ ለቃሉም አልታዛችሁም።


በዚህ ዓይነት የከነዓናውያን ድንበር ከሲዶና አንሥቶ፥ በገራር አጠገብ እስካለው እስከ ጋዛ ድረስ፥ ወደ ሰዶም እና ገሞራ፥ አዳማና በላሻዕ አጠገብ እስካለው እስከ ጸቦይም ድረስ ይደርሳል።


የጌታም መልአክ ፊልጶስን “ተነሥተህ በደቡብ በኩል ከኢየሩሳሌም ወደ ጋዛ ወደሚያወርደው ምድረ በዳ ወደ ሆነ መንገድ ሂድ፤” አለው።


አስቀሎና አይታ ትፈራለች፤ ጋዛ በሥጋት ትታመማለች፤ እንዲሁም አቃሮን፥ ተስፋዋ ይመነምናል። ንጉሡም ከጋዛ ይጠፋል፥ በአስቀሎናም የሚኖር አይገኝም።


በዚያች ሌሊት ጌታ በገባዖን ለሰሎሞን በሕልም ተገለጠለትና “ምን እንድሰጥህ ትፈልጋለህ?” አለው።


ፍልስጥኤማውያን ስለ በደል መሥዋዕት ለጌታ የላኳቸው የወርቅ ዕባጮች እነዚህ ናቸው፤ አንዱ ስለ አሽዶድ፥ አንዱ ስለ ጋዛ፥ አንዱ ስለ አስቀሎና፥ አንዱ ስለ ጌት፥ አንዱ ስለ ዔቅሮን የቀረቡ ነበሩ።


ከዚያም ፍልስጥኤማውያን ያዙት፤ ዐይኖቹን አውጥተው ወደ ጋዛ ይዘውት ወረዱ፤ በናስ ሰንሰለት አስረውም እስር ቤት ውስጥ እህል እንዲፈጭ አደረጉት፤


አንድ ቀን ሳምሶን ወደ ጋዛ ሄደ፤ እዚያም አንዲት ዝሙት አዳሪ አየ፤ አብሮአት ለማደርም ገባ።


ጌታም በእስራኤል ልጆች እጅ አሞራውያንን አሳልፎ በሰጠ ቀን ኢያሱ ለጌታ እንዲህ ብሎ ተናገረ፤ የእስራኤልም ልጆች እያዩ እንዲህ አለ፦ “በገባዖን ላይ ፀሐይ ትቁም፥ በኤሎንም ሸለቆ ጨረቃ፤”


ገባዖን ከመንግሥታት ከተሞች እንደ አንዲቱ ታላቅ ከተማ ስለ ነበረች፥ ከጋይም ስለ ምትበልጥ፥ ሰዎችዋም ሁሉ ኃያላን ስለ ነበሩ፥ እጅግ ፈራ።


ድንበራችሁም በአቅረቢም ዐቀበት በደቡብ በኩል ይዞራል ወደ ጺንም ይሻገራል፤ በቃዴስ በርኔ በደቡብ በኩል ያለው መጨረሻው ይሆናል፤ ወደ ሐጸርአዳር ይሄዳል ወደ ዓጽሞንም ያልፋል፤


ምድሪቱን እንዲሰልሉ ከቃዴስ በርኔ በላክኋቸው ጊዜ አባቶቻችሁ እንዲህ አደረጉ።


ተጉዘውም በፋራን ምድረ በዳ በቃዴስ ወዳሉት ወደ ሙሴና ወደ አሮን ወደ እስራኤልም ልጆች ማኅበር ሁሉ መጡ፤ ወሬውንም ለእነርሱና ለማኅበሩ ሁሉ ነገሩአቸው፥ የምድሪቱንም ፍሬ አሳዩአቸው።


“ከኮሬብም ወጣን፥ ጌታ አምላካችን እንዳዘዘን በታላቁ እጅግም በሚያስፈራ በዚያ ሁሉ ባያችሁት ምድረ በዳ በኩል በተራራማው በአሞራውያን መንገድ ሄድን፥ ወደ ቃዴስ በርኔም መጣን።


እስከ ጋዛም ድረስ በመንደሮች ተቀምጠው የነበሩትን ኤዋውያንን ከካፍቶር የወጡ ካፍቶራውያን አጠፉአቸው፥ በስፍራቸውም ሰፈሩ።


በጋዛ በጌትም በአዛጦንም ጥቂቶች ቀሩ እንጂ በእስራኤል ልጆች ምድር ከዔናቅ ልጆች ማንም አልቀረም።


Follow us:

Advertisements


Advertisements