Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ዮናስ 1:4 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

4 ጌታ ግን በባሕሩ ላይ ታላቅ ነፋስን አስነሣ፥ በባሕሩም ላይ ታላቅ ማዕበል ተነሣ፥ መርከቢቱም ልትሰበር ቀረበች።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

4 እግዚአብሔርም በባሕሩ ላይ ታላቅ ነፋስን ላከ፤ ከባድ ማዕበልም ተነሥቶ መርከቢቱን አንገላታት፤ ልትሰበርም ተቃረበች።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

4 እግዚአብሔር ግን በባሕሩ ላይ ከባድ ነፋስን አስነሣ፤ በባሕሩም ላይ የተቀሰቀሰው ማዕበል ብርቱ ከመሆኑ የተነሣ መርከቢቱ ልትሰበር ተቃረበች፤

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

4 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በባ​ሕሩ ላይ ታላቅ ነፋ​ስን አመጣ፤ በባ​ሕ​ሩም ላይ ታላቅ ማዕ​በል ሆነ፤ መር​ከ​ቢ​ቱም ልት​ሰ​በር ቀረ​በች።

See the chapter Copy




ዮናስ 1:4
13 Cross References  

“እነሆ፥ ተራሮችን የሠራ፥ ነፋስንም የፈጠረ፥ የልቡንም ሐሳብ ለሰው የሚነግር፥ ንጋትን ጨለማ የሚያደርግ፥ በምድርም ከፍታዎች ላይ የሚረግጥ፥ ስሙ የሠራዊት አምላክ ጌታ ነው።”


ከምድር ዳርቻ ደመናትን ያወጣል፥ በዝናብ ጊዜ መብረቅን ያደርጋል፥ ነፋሳትንም ከመዛግብቱ ያወጣል።


ጌታም ከምዕራብ ዐውሎ ነፋሱን መለሰ፥ አንበጣዎቹንም ወስዶ በኤርትራ ባሕር ውስጥ ጣላቸው፤ አንድ ስንኳ አንበጣ በግብጽ አገር አልቀረም።


ነፋስም ከጌታ ዘንድ ወጣ፥ ከባሕርም ድርጭቶችን አመጣ፥ እነርሱንም የአንድ ቀን መንገድ ያህል በዚህ፥ የአንድ ቀንም መንገድ ያህል በዚያ በሰፈሩ አጠገብ በተናቸው፤ በዚያም በሰፈሩ ዙሪያ ከፍታው ከምድር ወደ ላይ ሁለት ክንድ ያህል ቈለላቸው።


ትንፋሽህን እፍ አልክባቸው፥ ባሕርም ከደናቸው፤ በኃይለኞች ውኆችም እንደ ብረት ሰጠሙ።


ሙሴም በባሕሩ ላይ እጁን ዘረጋ፤ ጌታም ሌሊቱን ሁሉ ጽኑ የምሥራቅ ነፋስ አምጥቶ ባሕሩን አስወገደው፥ ባሕሩንም ደረቅ ምድር አደረገው፥ ውኆችም ተከፈሉ።


ሙሴም በግብጽ ምድር ላይ በትሩን ዘረጋ፥ ጌታም የምሥራቅን ነፋስ ያን ቀን ሁሉ ሌሊቱን ሁሉ አመጣ፤ በነጋም ጊዜ የምሥራቁ ነፋስ አንበጣዎቹን አመጣ።


በሰማይና በምድር በባሕርና በጥልቆች ሁሉ፥ ጌታ የወደደውን ሁሉ አደረገ።


ድምጹን ባሰማ ጊዜ ውኆች በሰማይ ይታወካሉ፥ ከምድርም ዳር ደመናትን ከፍ ያደርጋል፤ ለዝናብም መብረቅን ያደርጋል፥ ነፋስንም ከቤተ መዛግብቱ ያወጣል።


እሳትና በረዶ አመዳይና ጉም፥ ቃሉን የሚፈጽም ዐውሎ ነፋስም፥


Follow us:

Advertisements


Advertisements