Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ዮሐንስ 9:21 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

21 ዳሩ ግን አሁን እንዴት ማየት እንደቻለ አናውቅም፤ ወይም ዐይኖቹን ማን እንደ ከፈተለት እኛ አናውቅም፤ እርሱን ጠይቁት፤ እርሱ ሙሉ ሰው ነው፤ እርሱ ስለ እራሱ መናገር ይችላል፤” አሉ።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

21 አሁን ግን እንዴት ማየት እንደ ቻለና ዐይኖቹን ማን እንደ ከፈተለት እኛ አናውቅም። ሙሉ ሰው ስለ ሆነ፣ ስለ ራሱ መናገር ይችላልና እርሱን ጠይቁት።”

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

21 ነገር ግን አሁን እንዴት እንደሚያይና ዐይኖቹንም ማን እንደአበራለት አናውቅም፤ እርሱን ጠይቁት፤ እርሱ በዕድሜው ሙሉ ሰው ስለ ሆነ ስለ ራሱ መናገር ይችላል።”

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

21 አሁን ግን እን​ዴት እን​ደ​ሚ​ያይ ዐይ​ኖ​ቹ​ንም ማን እንደ አበ​ራ​ለት አና​ው​ቅም፤ እር​ሱን ጠይ​ቁት፤ ዐዋቂ ነውና፤ ስለ ራሱም መና​ገር ይች​ላ​ልና።”

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

21 ዳሩ ግን አሁን እንዴት እንዳየ አናውቅም፥ ወይም ዓይኖቹን ማን እንደ ከፈተ እኛ አናውቅም፤ ጠይቁት እርሱ ሙሉ ሰው ነው፤ እርሱ ስለ ራሱ ይናገራል” አሉ።

See the chapter Copy




ዮሐንስ 9:21
7 Cross References  

ወላጆቹም መልሰው “ይህ ልጃችን እንደሆነ ዐይነ ስውርም ሆኖ እንደ ተወለደ እናውቃለን፤


ወላጆቹ አይሁድን ስለ ፈሩ ይህንን አሉ፤ “እርሱ ክርስቶስ ነው፤” ብሎ የሚመሰክር ቢኖር ከምኵራብ እንዲያወጡት አይሁድ ከዚህ በፊት ተስማምተው ነበርና።


ስለዚህ ወላጆቹ “ሙሉ ሰው ነው፤ እርሱን ጠይቁት፤” አሉ።


ከዐሥራ ሁለት ዓመትም ጀምሮ ደም የሚፈሳት ሴት ነበረች፤ ያላትንም ንብረት ሁሉ ተጠቅማ ለባለመድኃኒቶች ብታውልም ማንም ሊፈውሳት አልተቻለውም።


በዚያም ከሠላሳ ስምንት ዓመት ጀምሮ የታመመ አንድ ሰው ነበረ፤


ታድያ “ዐይኖችህ እንዴት ተከፈቱ?” አሉት።


በዚያም ከስምንት ዓመት ጀምሮ በአልጋ ላይ ተኝቶ የነበረውን ኤንያ የሚሉትን አንድ ሰው አገኘ፤ እርሱም ሽባ ነበረ።


Follow us:

Advertisements


Advertisements