Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ዮሐንስ 9:11 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

11 እርሱ መልሶ “ኢየሱስ የሚባለው ሰው ጭቃ አድርጎ ዐይኖቼን ቀባና ‘ወደ ሰሊሆም መጠመቂያ ሄደህ ታጠብ፤’ አለኝ፤ ሄጄ ታጥቤም አየሁ፤” አለ።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

11 እርሱም፣ “ኢየሱስ የሚሉት ሰው ጭቃ አድርጎ ዐይኔን ቀባኝ፤ ወደ ሰሊሆም ሄጄ እንድታጠብም ነገረኝ፤ ሄጄ ታጠብሁ፤ ማየትም ቻልሁ” ሲል መለሰ።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

11 እርሱም “ኢየሱስ የተባለ ሰው ጭቃ ለውሶ ዐይኖቼን ቀባና ‘ወደ ሰሊሆም ሄደህ ታጠብ’ አለኝ፤ እኔም ሄጄ ታጠብኩና ለማየት ቻልኩ” ሲል መለሰ።

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

11 እር​ሱም መልሶ፥ “ኢየ​ሱስ የሚ​ባ​ለው ሰው በም​ራቁ ጭቃ አድ​ርጎ ዐይ​ኖ​ችን ቀባ​ኝና ሂደህ በሰ​ሊ​ሆም ውኃ ታጠብ አለኝ፤ ሄጄም ታጠ​ብ​ሁና አየሁ” አላ​ቸው።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

11 እርሱ መልሶ፦ “ኢየሱስ የሚባለው ሰው ጭቃ አድርጎ አይኖቼን ቀባና፦ ‘ወደ ሰሊሆም መጠመቂያ ሄደህ ታጠብ’ አለኝ፤ ሄጄ ታጥቤም አየሁ” አለ።

See the chapter Copy




ዮሐንስ 9:11
6 Cross References  

እርሱም መልሶ “አስቀድሜ ነገርኋችሁ፤ አልሰማችሁምም፤ ስለምን ዳግመኛ ልትሰሙ ትፈልጋላችሁ? እናንተ ደግሞ ደቀመዛሙርቱ ልትሆኑ ትፈልጋላችሁን?” አላቸው።


ባሮክንም፦ “እነዚህን ሁሉ ቃላት እንዴት እንደ ጻፍከው እስኪ ንገረን፤ እርሱ እየነገረህ ነውን?” ብለው ጠየቁት።


ወይንስ በሰሊሆም ግንቡ የወደቀባቸውና የገደላቸው እነዚያ ዐሥራ ስምንት ሰዎች በኢየሩሳሌም ከሚኖሩት ሁሉ ይልቅ በደለኞች ይመስሉአችኋልን? አይደለም፥ እላችኋለሁ፤


ታድያ “ዐይኖችህ እንዴት ተከፈቱ?” አሉት።


“ያ ሰው ወዴት ነው?” አሉት። “አላውቅም” አለ።


Follow us:

Advertisements


Advertisements