ዮሐንስ 8:28 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)28 ስለዚህም ኢየሱስ “የሰውን ልጅ ከፍ ከፍ ባደረጋችሁት ጊዜ እኔ እንደሆንሁ፥ እንደዚህም የምናገረው አባቴ እንዳስተማረኝ እንጂ በእራሴ ምንም እንደማላደርግ በዚያን ጊዜ ታውቃላችሁ። See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም28 ስለዚህ ኢየሱስ እንዲህ አለ፤ “የሰው ልጅን ከፍ ከፍ ባደረጋችሁት ጊዜ፣ ያ ያልሁት እርሱ እኔ እንደ ሆንሁና አብ ያስተማረኝን እንደምናገር፣ በራሴም ፈቃድ ምንም እንደማላደርግ ታውቃላችሁ፤ See the chapterአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም28 ስለዚህ ኢየሱስ እንዲህ አላቸው፦ “የሰውን ልጅ ከፍ አድርጋችሁ በምትሰቅሉት ጊዜ እኔ እርሱ እንደ ሆንኩ ታውቃላችሁ፤ እንዲሁም አብ ያስተማረኝን እንደምናገር እንጂ በራሴ ሥልጣን ብቻ ምንም እንደማላደርግ ያን ጊዜ ታስተውላላችሁ። See the chapterየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)28 ጌታችን ኢየሱስም እንዲህ አላቸው፥ “የሰውን ልጅ ከፍ ከፍ በአደረጋችሁት ጊዜ እኔ እንደ ሆንሁ ያንጊዜ ታውቃላችሁ፤ አባቴ እንደ አስተማረኝም እንዲሁ እናገራለሁ እንጂ የምናገረው ከእኔ አይደለም። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)28 ስለዚህም ኢየሱስ፦ “የሰውን ልጅ ከፍ ከፍ ባደረጋችሁት ጊዜ እኔ እሆን ዘንድ አባቴም እንዳስተማረኝ እነዚህን እናገር ዘንድ እንጂ ከራሴ አንዳች እንዳላደርግ በዚያን ጊዜ ታውቃላችሁ። See the chapter |