Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ዮሐንስ 7:4 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

4 በይፋ መታወቅ እየፈለገ በስውር የሚሠራ የለምና። እነዚህን ነገሮች የምታደርግ ከሆነ እራስህን ለዓለም ግለጥ፤” አሉት።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

4 ራሱን ሊገልጥ እየፈለገ በስውር የሚሠራ ማንም የለምና። አንተም እነዚህን ነገሮች የምታደርግ ከሆነ፣ ራስህን ለዓለም ግለጥ።”

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

4 በግልጥ ለመታወቅ የሚፈልግ ሰው ሥራውን በስውር አያደርግም፤ አንተም እነዚህን ነገሮች ሁሉ ስታደርግ ራስህን ለዓለም ልትገልጥ ያስፈልጋል።”

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

4 ሊገ​ለጥ ወድዶ ሳለ በስ​ውር አን​ዳች ነገር የሚ​ያ​ደ​ርግ ማንም የለ​ምና፤ አንተ ግን ይህን የም​ታ​ደ​ርግ ከሆነ ራስ​ህን ለዓ​ለም ግለጥ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

4 ራሱ ሊገልጥ እየፈለገ በስውር የሚሠራ የለምና። እነዚህን ብታደርግ ራስህን ለዓለም ግለጥ” አሉት።

See the chapter Copy




ዮሐንስ 7:4
12 Cross References  

ኢየሱስም መልሶ “እኔ በግልጥ ለዓለም ተናገርሁ፤ አይሁድ ሁሉ በሚሰበሰቡበት በምኵራብና በመቅደስ ሁልጊዜ አስተማርሁ፤ በስውርም ምንም አልተናገርሁም።


መልካም ሰው በልቡ ከሚገኘው መልካም መዝገብ መልካሙን ያወጣል፤ ክፉ ሰውም በልቡ ከሚገኘው ክፉ መዝገብ ክፉውን ያወጣል፤ በልብ ሞልቶ ከተረፈው አፉ ይናገራልና።


ሥራቸውን ሁሉ የሚያደርጉት ሰው እንዲያይላቸው ነው፤ ስለዚህ አሽንክታባቸውን ያሰፋሉ፤ የልብሳቸውንም ዘርፍ ያስረዝማሉ፤


“ስትጸልዩ እንደ ግብዞች አትሁኑ፤ በሰዎች ለመታየት ሲሉ በየምኵራቡ ና በየመንገዱ ማዕዘን ቆመው መጸለይን ይወዳሉና፤ እውነት እላችኋለሁ፤ ዋጋቸውን ተቀብለዋል።


“ስትጾሙ እንደ ግብዞች አትጠውልጉ፤ ሰዎች መጾማቸውን እንዲያዩላቸው ፊታቸውን ይለውጣሉና፤ እውነት እላችኋለሁ ዋጋቸውን ተቀብለዋል።


“‘መላእክቱን ስለ አንተ ያዝልሃል፤ እግርህም በድንጋይ ከቶ እንዳትሰናከል በእጃቸው ያነሡሃል’ ተብሎ ተጽፎአልና የእግዚአብሔር ልጅ ከሆንህ፥ ራስህን ወደ ታች ወርውር” አለው።


ሚክያስን ለመጥራት ሄዶ የነበረው መልእክተኛ በዚሁ ጊዜ ሚክያስን “ሌሎቹ ነቢያት በሙሉ ንጉሥ አክዓብ ድል የሚያደርግ መሆኑን የሚያረጋግጥ የትንቢት ቃል ተናግረዋል፤ ስለዚህም አንተም እንደ እነርሱ ብታደርግ ይሻልሃል” አለው።


ወንድሞቹም “ደቀ መዛሙርትህ ደግሞ የምታደርገውን ሥራ እንዲያዩ ከዚህ ተነሣና ወደ ይሁዳ ሂድ፤


ወንድሞቹም እንኳን አላመኑበትም ነበርና።


Follow us:

Advertisements


Advertisements