Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ዮሐንስ 7:36 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

36 ‘ትፈልጉኛላችሁ አታገኙኝምም፤ እኔም ወዳለሁበት እናንተ ልትመጡ አትችሉም፤’ የሚለውስ ይህ አባባል ምን ማለት ነው?”

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

36 ‘ትፈልጉኛላችሁ፤ ግን አታገኙኝም፤ እኔ ወዳለሁበትም ልትመጡ አትችሉም’ ሲል ምን ማለቱ ይሆን?”

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

36 ‘ትፈልጉኛላችሁ፤ ነገር ግን አታገኙኝም፤ እኔ ወዳለሁበት እናንተ ልትመጡ አትችሉም’ ሲል ምን ማለቱ ነው?”

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

36 ‘ትሹ​ኛ​ላ​ችሁ፤ አታ​ገ​ኙ​ኝ​ምም፤ እኔ ወደ​ም​ሄ​ድ​በት እና​ንተ መም​ጣት አት​ች​ሉም’ የሚ​ለን ይህ ነገር ምን​ድን ነው?”

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

36 እርሱ፦ “ትፈልጉኛላችሁ አታገኙኝምም እኔም ወዳለሁበት እናንተ ልትመጡ አትችሉም የሚለው ይህ ቃል ምንድር ነው?” ብለው እርስ በርሳቸው ተነጋገሩ።

See the chapter Copy




ዮሐንስ 7:36
11 Cross References  

ኒቆዲሞስ መልሶ “ይህ እንዴት ሊሆን ይችላል?” አለው።


ትፈልጉኛላችሁ አታገኙኝም፤ እኔም ወዳለሁበት እናንተ ልትመጡ አትችሉም፤” አለ።


ፍጥረታዊ ሰው ግን የእግዚአብሔርን መንፈስ ነገር አይቀበለውም፤ ይህ ለእርሱ ሞኝነት ነው፥ ምክንያቱም በመንፈስ የሚመረመር ነውና፥ ሊያውቀው አይችልም።


እንዲህ ሕዝቡ “እኛስ ክርስቶስ ለዘለዓለም እንዲኖር ከሕጉ ሰምተናል፤ አንተስ የሰው ልጅ ከፍ ከፍ ይል ዘንድ እንዲያስፈልገው እንዴት ትላላህ? ይህ የሰው ልጅ ማን ነው?” ብለው መለሱለት።


ከደቀ መዛሙርቱም ብዙዎቹ በሰሙ ጊዜ “ይህ ንግግር ከባድ ነው፤ ማን ሊሰማው ይችላል?” አሉ።


አይሁድም “ይህ ሰው ሥጋውን እንድንበላ እንዴት ሊሰጠን ይችላል?” ብለው እርስ በርሳቸው ተከራከሩ።


አይሁድም “ከሰማይ የወረደ እንጀራ እኔ ነኝ፤” በማለቱ ማንጐራጐር ጀመሩ፤


ኒቆዲሞስም “ሰው ከሸመገለ በኋላ እንዴት ሊወለድ ይችላል? ዳግመኛ ወደ እናቱ ማኅፀን ገብቶ መወለድ ይችላልን?” አለው።


ኢየሱስም ደግሞ “እኔ እሄዳለሁ፤ ትፈልጉኛላችሁም፤ በኀጢአታችሁም ትሞታላችሁ፤ እኔ ወደምሄድበት እናንተ ልትመጡ አትችሉም፤” አላቸው።


ልጆች ሆይ! ገና ጥቂት ጊዜ ከእናንተ ጋር ነኝ፤ ትፈልጉኛላችሁ፤ ለአይሁድም ‘እኔ ወደምሄድበት እናንተ ልትመጡ አትችሉም፤’ እንዳልኋቸው፥ አሁን ለእናንተ ደግሞ እላችኋለሁ።


Follow us:

Advertisements


Advertisements