Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ዮሐንስ 6:24 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

24 ሕዝቡም ኢየሱስ ወይም ደቀመዛሙርቱ በዚያ እንዳልነበሩ ባዩ ጊዜ፥ እራሳቸው በጀልባዎቹ ገብተው ኢየሱስን እየፈለጉ ወደ ቅፍርናሆም መጡ።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

24 ሰዎቹም፣ ኢየሱስ ወይም ደቀ መዛሙርቱ በዚያ አለመኖራቸውን እንዳወቁ፣ ኢየሱስን ፍለጋ በጀልባዎቹ ወደ ቅፍርናሆም ሄዱ።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

24 ሰዎቹም ኢየሱስ ወይም ደቀ መዛሙርቱ በእዚያ እንደሌሉ ባዩ ጊዜ በነዚያ ጀልባዎች ተሳፍረው ኢየሱስን ፍለጋ ወደ ቅፍርናሆም ሄዱ።

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

24 እነ​ዚያ ሰዎ​ችም ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ፥ ደቀ መዛ​ሙ​ር​ቱም በዚያ እን​ዳ​ል​ነ​በሩ ባዩ ጊዜ ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስን ይፈ​ል​ጉት ዘንድ በእ​ነ​ዚያ ታን​ኳ​ዎች ገብ​ተው ወደ ቅፍ​ር​ና​ሆም መጡ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

24 ሕዝቡም ኢየሱስ ወይም ደቀ መዛሙርቱ በዚያ እንዳልነበሩ ባዩ ጊዜ፥ ራሳቸው በጀልባዎቹ ገብተው ኢየሱስን እየፈለጉ ወደ ቅፍርናሆም መጡ።

See the chapter Copy




ዮሐንስ 6:24
11 Cross References  

በታንኳም ገብተው በባሕር ማዶ ወደ ቅፍርናሆም ይመጡ ነበር። ከወዲሁ ጨልሞ ነበር፤ ኢየሱስም ገና ወደ እነርሱ አልመጣም ነበር፤


ባገኙትም ጊዜ፥ “ሰዉ ሁሉ ይፈልግሃል” አሉት።


ኢየሱስም “አንቺ ሴት! ስለምን ታለቅሻለሽ? ማንንስ ትፈልጊያለሽ?” አላት። እርሷም የአትክልት ጠባቂ መስሎአት “ጌታ ሆይ! አንተ ወስደኸው እንደሆንህ ወዴት እንዳኖርኸው ንገረኝ፤ እኔም እወስደዋለሁ፤” አለችው።


አይሁድም “እርሱ ወዴት ነው?” እያሉ በበዓሉ ይፈልጉት ነበር።


በቅፍርናሆም፥ በምኵራብ ሲያስተምር ነበር ይህን ያለው።


ዳሩ ግን ሌሎች ጀልባዎች ጌታ የባረከውን እንጀራ ወደ በሉበት ስፍራ አጠገብ ከጥብርያዶስ መጡ።


ሕዝቡም ሁሉ እየጠበቁት ስለ ነበር ኢየሱስ በተመለሰ ጊዜ ተቀበሉት።


በተሻገሩም ጊዜ፥ ጌንሴሬጥ ደርሰው ወረዱ፤ ጀልባዋንም እዚያው አቆሙ።


ተሻግረውም ወደ ጌንሴሬጥ ምድር መጡ።


ኢየሱስም መልሶ “እውነት እውነት እላችኋለሁ፤ የምትፈልጉኝ እንጀራን ስለ በላችሁና ስለ ጠገባችሁ ነው እንጂ ምልክቶችን ስላያችሁ አይደለም።


Follow us:

Advertisements


Advertisements