ዮሐንስ 6:22 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)22 በማግሥቱም በባሕር ማዶ ቆሞ የነበረው ሕዝብ ከአንዲት ጀልባ በቀር በዚያ ሌላ ጀልባ እንዳልነበረች፥ ደቀ መዛሙርቱም ለብቻቸው እንደ ሄዱ እንጂ ኢየሱስ ከደቀ መዛሙርቱ ጋር ወደ ታንኳይቱ እንዳልገባ አዩ፤ See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም22 በማግስቱም በባሕሩ ማዶ የቀሩት ሰዎች በዚያ አንዲት ጀልባ ብቻ እንደ ነበረች ተረዱ፤ ኢየሱስ እንዳልተሳፈረና ደቀ መዛሙርቱ ብቻቸውን እንደ ሄዱም ዐወቁ። See the chapterአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም22 በማግስቱ ከባሕሩ ማዶ ቀርተው የነበሩት ሰዎች፥ በባሕሩ ላይ አንድ ጀልባ ብቻ እንደ ነበረና በዚያም ደቀ መዛሙርቱ ብቻቸውን እንደ ሄዱ፥ ኢየሱስ ግን ከእነርሱ ጋር ወደ ጀልባዋ እንዳልገባ አይተው ነበር። See the chapterየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)22 በማግሥቱም ከባሕሩ ዳር ቆመው የነበሩ ሰዎች ከአንዲት ታንኳ በቀር ከዚያ ሌላ ታንኳ እንዳልነበረ፥ ደቀ መዛሙርቱም ለብቻቸው ሄዱ እንጂ ጌታችን ኢየሱስ ከደቀ መዛሙርቱ ጋር ወደ ታንኳ እንዳልወጣ አዩ። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)22 በነገው በባሕር ማዶ ቆመው የነበሩ ሕዝቡ ከአንዲት ጀልባ በቀር በዚያ ሌላ ጀልባ እንዳልነበረች፥ ደቀ መዛሙርቱም ለብቻቸው እንደ ሄዱ እንጂ ኢየሱስ ከደቀ መዛሙርቱ ጋር ወደ ታንኳይቱ እንዳልገባ አዩ፤ See the chapter |