ዮሐንስ 4:27 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)27 በዚያም ጊዜ ደቀመዛሙርቱ መጡና ከሴት ጋር በመነጋገሩ ተደነቁ፤ ነገር ግን “ምን ፈለግህ?” ወይም “ስለምን ትናገራታለህ?” ያለ ማንም አልነበረም። See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም27 በዚህ ጊዜ ደቀ መዛሙርቱ ተመልሰው መጡ፤ ከሴት ጋራ ሲነጋገር በማግኘታቸው ተደነቁ፤ ሆኖም ግን፤ “ምን ፈለግህ?” ወይም፣ “ከርሷ ጋራ የምትነጋገረው ለምንድን ነው?” ብሎ የጠየቀው ማንም አልነበረም። See the chapterአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም27 በዚህ ጊዜ ደቀ መዛሙርቱ ከሄዱበት ተመልሰው መጡ፤ ኢየሱስ ከሴት ጋር በመነጋገሩ ተገረሙ፤ ይሁን እንጂ “ምን ትፈልጋለህ? ወይም ከእርስዋ ጋር ለምን ትነጋገራለህ?” ብሎ የጠየቀው ማንም አልነበረም። See the chapterየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)27 በዚያም ጊዜ ደቀ መዛሙርቱ መጡ፤ ከሴት ጋርም ይነጋገር ነበርና ተደነቁ፤ ነገር ግን፥ “ምን ትሻለህ? ወይስ ከእርስዋ ጋር ለምን ትነጋገራለህ?” ያለው የለም። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)27 በዚያም ጊዜ ደቀ መዛሙርቱ መጡና ከሴት ጋር በመነጋገሩ ተደነቁ፤ ነገር ግን፦ ምን ትፈልጊያለሽ? ወይም፦ ስለ ምን ትናገራታለህ? ያለ ማንም አልነበረም። See the chapter |