ዮሐንስ 21:25 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)25 ኢየሱስም ያደረገው ሌላ ብዙ ነገር አለ፤ ሁሉም አንድ በአንድ ቢጻፍ፥ እንደሚመስለኝ፥ ዓለም እራሱ የሚጻፉትን መጻሕፍት ለመያዝ ቦታ አይበቃውም ነበር። See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም25 ኢየሱስ ያደረጋቸው ሌሎችም ብዙ ነገሮች አሉ፤ ሁሉም ነገር ቢጻፍ፣ ለተጻፉት መጻሕፍት ሁሉ ዓለም በቂ ቦታ የሚኖረው አይመስለኝም። See the chapterአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም25 ኢየሱስ ያደረጋቸው ሌሎች ብዙ ነገሮች ደግሞ አሉ። እኔ እንደሚመስለኝ እርሱ ያደረጋቸው ነገሮች ሁሉ አንድ በአንድ ቢጻፉ ኖሮ የሚጻፉትን መጻሕፍት ዓለም ራሱ መሸከም ባልቻለም ነበር። See the chapterየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)25 ጌታችን ኢየሱስ የሠራቸው ሌሎች ብዙ ሥራዎች አሉ፤ ሁሉ እያንዳንዱ ቢጻፍ ግን የተጻፉትን መጻሕፍት ዓለም ስንኳን ባልቻላቸውም ነበር። ከዐሥራ ሁለቱ ሐዋርያት አንዱ የዘብዴዎስ ልጅ ሐዋርያው ዮሐንስ ጌታችን በሥጋ ወደ ሰማይ ባረገ በሠላሳ ዓመት፥ ቄሳር ኔሮን በነገሠ በሰባት ዓመት በዮናናውያን ቋንቋ ለኤፌሶን ሰዎች የጻፈፍው ወንጌል ተፈጸመ። ምስጋና ለእግዚአብሔር ይሁን። አሜን። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)25 ኢየሱስም ያደረገው ብዙ ሌላ ነገር ደግሞ አለ፤ ሁሉ በእያንዳንዱ ቢጻፍ ለተጻፉት መጻሕፍት ዓለም ራሱ ባልበቃቸውም ይመስለኛል። See the chapter |