ዮሐንስ 20:1 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)1 ከሳምንቱም በመጀመሪያው ቀን መግደላዊት ማርያም ገና ጨለሞ ሳለ በማለዳ ወደ መቃብር መጣች፤ ድንጋዩም ከመቃብሩ ተፈንቅሎ አየች። See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም1 በሳምንቱ የመጀመሪያ ቀን፣ በማለዳ ገና ጨለማ ሳለ፣ መግደላዊት ማርያም ወደ መቃብሩ ሄደች፤ ድንጋዩም ከመቃብሩ ተንከባልሎ አየች። See the chapterአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም1 እሑድ ጠዋት በማለዳ፥ ገና ጎሕ ሳይቀድ፥ መግደላዊት ማርያም ወደ ኢየሱስ መቃብር ሄደች፤ እዚያም እንደ ደረሰች መቃብሩ ተዘግቶበት የነበረው ድንጋይ ከመቃብሩ በር ላይ ተነሥቶ አየች። See the chapterየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)1 ከሳምንቱም በመጀመሪያዉ ቀን ማርያም መግደላዊት በማለዳ ገና ጨለማ ሳለ ወደ መቃብር መጣች፤ ድንጋዩንም ከመቃብሩ አፍ ተነሥቶ አገኘችው። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)1 ከሳምንቱም በፊተኛው ቀን መግደላዊት ማርያም ገና ጨለማ ሳለ ማለዳ ወደ መቃብር መጣች ድንጋዩም ከመቃብሩ ተፈንቅሎ አየች። See the chapter |