Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ዮሐንስ 2:20 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

20 ስለዚህ አይሁድ “ይህ ቤተ መቅደስ ለአርባ ስድስት ዓመት እየተሠራ ነበር፤ አንተስ በሦስት ቀን ታነሣዋለህን?” አሉት።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

20 አይሁድም፣ “ይህን ቤተ መቅደስ ለመሥራት አርባ ስድስት ዓመት ፈጅቷል፤ ታዲያ አንተ እንዴት በሦስት ቀን መልሰህ ታነሣዋለህ?” አሉት።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

20 እነርሱም “ይህን ቤተ መቅደስ ለመሥራት አርባ ስድስት ዓመት ፈጅቶአል፤ ታዲያ አንተ በሦስት ቀን ውስጥ ትሠራዋለህን?” አሉት።

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

20 አይ​ሁ​ድም፥ “ይህ ቤተ መቅ​ደስ በአ​ርባ ስድ​ስት ዓመት ተሠራ፤ አን​ተስ በሦ​ስት ቀኖች ውስጥ ታነ​ሣ​ዋ​ለ​ህን?” አሉት።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

20 ስለዚህ አይሁድ፦ ይህ ቤተ መቅደስ ከአርባ ስድስት ዓመት ጀምሮ ይሠራ ነበር፥ አንተስ በሦስት ቀን ታነሣዋለህን? አሉት።

See the chapter Copy




ዮሐንስ 2:20
6 Cross References  

በዚያን ጊዜ ይህ ሼሽባጻር መጣ፥ በኢየሩሳሌምም ያለውን የእግዚአብሔርን ቤት መሠረተ፤ ከዚያም ጊዜ ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ እየተሠራ ነው አላለቀምም።


አይሁድም “አንተ ማን ነህ?” ብለው ለመጠየቅ ከኢየሩሳሌም ካህናትንና ሌዋውያንን በላኩበት ጊዜ፥ የዮሐንስ ምስክርነት ይህ ነው።


ተቀበረ፤ በቅዱሳት መጻሕፍት እንደተጻፈውም በሦስተኛው ቀን ተነሣ፤


ሰሎሞን በነገሠ በዐሥራ አንደኛ ዓመቱ፥ ቡል ተብሎ በሚጠራው በስምንተኛው ወር ላይ የቤተ መቅደሱ ሥራ ልክ በታቀደው መሠረት ሙሉ በሙሉ ተጠናቀቀ፤ ሰሎሞን ቤተ መቅደሱን ለመሥራት የፈጀበት ጊዜ ሰባት ዓመት ነበር።


ኢየሱስ ከቤተ መቅደስ ወጥቶ ሲሄድ ደቀመዛሙርቱ የቤተ መቅደሱን ግንቦች ሊያሳዩት ወደ እርሱ ቀረቡ።


አንዳንዶቹም ስለ ቤተ መቅደስ በመልካም ድንጋይና በተሰጠው ሽልማት እንዳጌጠ ሲነጋገሩ


Follow us:

Advertisements


Advertisements