Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ዮሐንስ 18:26 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

26 ከሊቀ ካህናቱ አገልጋዮች መካከል አንዱ፥ ጴጥሮስ ጆሮውን የቈረጠው ሰው ዘመድ፥ “በአትክልቱ ስፍራ ከእርሱ ጋር አይቼህ አልነበረምን?” አለው።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

26 ከሊቀ ካህናቱ ባሮች አንዱ ጴጥሮስ ጆሮውን የቈረጠው ሰው ዘመድ፣ “በአትክልቱ ስፍራ አንተን ከርሱ ጋራ አላየሁህም?” ሲል ጠየቀው።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

26 ጴጥሮስ ጆሮውን የቈረጠው ሰው ዘመዱ የሆነው ከካህናት አለቃው ሎሌዎች አንዱ “በአትክልቱ ቦታ ከእነርሱ ጋር አይቼህ አልነበረምን?” አለው።

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

26 ጴጥ​ሮስ ጆሮ​ውን ከቈ​ረ​ጠው ሰው ዘመ​ዶች ወገን የሆነ ከሊቀ ካህ​ናቱ አገ​ል​ጋ​ዮ​ችም አንድ ሰው፥ “እኔ በአ​ት​ክ​ልት ቦታ ውስጥ ከእ​ርሱ ጋር አይ​ችህ አል​ነ​በ​ረ​ምን?” አለው።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

26 ጴጥሮስ ጆሮውን የቈረጠው ዘመድ የሆነ ከሊቀ ካህናቱ ባሮች አንዱ፦ “በአትክልቱ ከእርሱ ጋር እኔ አይቼህ አልነበረምን?” አለው።

See the chapter Copy




ዮሐንስ 18:26
7 Cross References  

ስምዖን ጴጥሮስም ሰይፍ ይዞ ስለ ነበር መዘዘውና የሊቀ ካህናቱን አገልጋይ መትቶ ቀኝ ጆሮውን ቈረጠ፤ የአገልጋዩም ስም ማልኮስ ነበረ።


ኢየሱስም ይህን ብሎ አትክልት ወዳለበት ስፍራ ወደ ቄድሮን ወንዝ ማዶ ከደቀ መዛሙርቱ ጋር ወጣ፤ እርሱም ደቀ መዛሙርቱም በዚያ ገቡ።


ከጥቂት ጊዜ በኋላ በዚያ ቆመው የነበሩት ጠጋ ብለው ጴጥሮስን “በእውነት አንተም ከእነርሱ ወገን ነህ፤ አነጋገርህ ያስታውቅብሃልና” አሉት።


የእውነት ከንፈር ለዘለዓለም ትቆማለች፥ ውሸተኛ ምላስ ግን ለቅጽበት ነው።


ከጥቂት ጊዜም በኋላ ሌላ ሰው አይቶት “አንተም እኮ ከእነርሱ አንዱ ነህ፤” አለው። ጴጥሮስ ግን “አንተ ሰው! አይደለሁም፤” አለ።


Follow us:

Advertisements


Advertisements