Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ዮሐንስ 16:14 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

14 እርሱ ያከብረኛል፤ የእኔ ከሆነው ወስዶ ይነግራችኋልና።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

14 የእኔ ከሆነው ወስዶ እንድታውቁ በማድረግ ያከብረኛል።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

14 የእኔ ከሆነው ወስዶ ስለሚነግራችሁ እኔን ያከብረኛል።

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

14 እር​ሱም እኔን ያከ​ብ​ረ​ኛል፤ ከእኔ ወስዶ ይነ​ግ​ራ​ች​ኋ​ልና።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

14 እርሱ ያከብረኛል፥ ከእኔ ካለኝ ወስዶ ይነግራችኋልና።

See the chapter Copy




ዮሐንስ 16:14
20 Cross References  

ዳሩ ግን እኔ ከአብ ዘንድ የምልክላችሁ አጽናኝ፥ እርሱም ከአብ የሚወጣው የእውነት መንፈስ በመጣ ጊዜ፥ እርሱ ስለ እኔ ይመሰክራል፤


ልሰግድለትም በእግሩ ፊት ተደፋሁ። እርሱም “እንዳታደርገው ተጠንቀቅ፤ ከአንተ ጋር የኢየሱስም ምስክርነት ከሚጠብቁት ከወንድሞችህ ጋር አብሬ ባርያ ነኝ፤ ለእግዚአብሔር ስገድ፤ የኢየሱስ ምስክርነት የትንቢት መንፈስ ነውና፤” አለኝ።


እኛ በመንፈስ፥ በእምነት፥ የጽድቅን ተስፋ እንጠባበቃለንና።


በክርስቶስ ፊት የእግዚአብሔርን የክብሩን እውቀት እንዲሰጥ ብርሃን በልባችን ውስጥ ያበራ፥ “በጨለማ ብርሃን ይብራ፤” ያለው እግዚአብሔር ነው።


ስለዚህ ማንም በእግዚአብሔር መንፈስ ሲናገር “ኢየሱስ የተረገመ ነው፤” የሚል እንደሌለ፥ በመንፈስ ቅዱስም ካልሆነ በቀር “ኢየሱስ ጌታ ነው፤” ሊል ማንም እንደማይችል አስታውቃችኋለሁ።


የእግዚአብሔር ልጅ እንደመጣ፥ እውነት የሆነውን እንድናውቅ ማስተዋልን እንደ ሰጠን እናውቃለን፤ እውነት በሆነው በእርሱ እንኖራለን፥ እርሱም ልጁ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። እርሱ እውነተኛ አምላክና የዘለዓለም ሕይወት ነው።


በውኃና በደም የመጣው ይህ ነው፥ ኢየሱስ ክርስቶስ፥ በውኃው ብቻ አይደለም ነገር ግን በውኃና በደም ነው። የሚመሰክረውም መንፈሱ ነው፥ መንፈሱ እውነት ነውና።


ትእዛዚቱም ይህች ናት፥ በልጁ በኢየሱስ ክርስቶስ ሥም እንድናምንና፥ እርሱም እንዳዘዘን እርስ በርሳችን እንድንዋደድ ነው።


ይህንንም በእርሱ የሚያምኑ ስለሚቀበሉት መንፈስ ተናገረ፤ ኢየሱስ ገና ስላልከበረ መንፈስ ገና አልወረደም ነበርና።


እንግዲህ ለእናንተ ለምታምኑት ይህ ድንጋይ ክቡር ነው፤ ለማያምኑት ግን “ግንበኞች የናቁት ድንጋይ እርሱ የማእዘን ራስ ሆነ።”


በዳዊት ቤት ላይ፥ በኢየሩሳሌምም በሚኖሩት ላይ፥ የምሕረትንና የልመናን መንፈስ አፈስሳለሁ። እነርሱም ወደ እርሱ በሚመለከቱበት ጊዜ የወጉትን ይመለከታሉ። ሰውም ለአንድ ልጁ እንደሚያለቅስ ያለቅሱለታል፥ ሰውም ለበኩር ልጁ እንደሚያዝን በመራራ ኅዘን ያዝኑለታል።


ትእዛዜ በእርሱ ዘንድ ያለችው የሚጠብቃትንም የሚወደኝ እርሱ ነው፤ የሚወደኝንም አባቴ ይወደዋል፤ እኔም እወደዋለሁ ራሴንም እገልጥለታለሁ።”


Follow us:

Advertisements


Advertisements