ዮሐንስ 13:26 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)26 ኢየሱስም “እኔ የእንጀራ ቁራሽ አጥቅሼ የምሰጠው እርሱ ነው” ብሎ መለሰለት። ቁራሽም አጥቅሶ ለአስቆሮቱ ለስምዖን ልጅ ለይሁዳ ሰጠው። See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም26 ኢየሱስም፣ “ይህን ቍራሽ እንጀራ ከወጭቱ አጥቅሼ የምሰጠው እርሱ ነው” አለው፤ ከዚያም ቍራሹን እንጀራ አጥቅሶ ለስምዖን ልጅ ለአስቆሮቱ ይሁዳ ሰጠው። See the chapterአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም26 ኢየሱስም “እርሱ ይህን እንጀራ በወጥ አጥቅሼ የማጐርሰው ነው” አለ። ይህንንም ብሎ እንጀራ በወጥ አጠቀሰና የአስቆሮታዊው ስምዖን ልጅ ለሆነው ለይሁዳ አጐረሰው። See the chapterየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)26 ጌታችን ኢየሱስም መልሶ፥ “ይህ እኔ እንጀራ በወጥ አጥቅሼ የምሰጠው ነው” አለው፤ ያን ጊዜም እንጀራ በወጥ አጥቅሶ ለስምዖን ልጅ ለአስቆሮታዊው ይሁዳ ሰጠው። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)26 ኢየሱስም፦ “እኔ ቍራሽ አጥቅሼ የምሰጠው እርሱ ነው” ብሎ መለሰለት። ቍራሽም አጥቅሶ ለአስቆሮቱ ለስምዖን ልጅ ለይሁዳ ሰጠው። See the chapter |