ዮሐንስ 12:38 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)38 ይህም ነቢዩ ኢሳይያስ “ጌታ ሆይ! ማን ምስክርነታችንን አመነ? የእግዚአብሔርስ ክንድ ለማን ተገለጠ?” ብሎ የተናገረው ቃል እንዲፈጸም ነው። See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም38 ይኸውም ነቢዩ ኢሳይያስ፣ “ጌታ ሆይ፤ መልእክታችንን ማን አምኗል? የጌታስ ክንድ ለማን ተገልጧል?” ያለው ቃል እንዲፈጸም ነው። See the chapterአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም38 ይህም የሆነው ነቢዩ ኢሳይያስ፥ “ጌታ ሆይ! ምስክርነታችንን ማን አመነ? የጌታስ ኀይል ለማን ተገለጠ?” ሲል የተናገረው ቃል እንዲፈጸም ነው። See the chapterየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)38 “አቤቱ፥ ምስክርነታችንን ማን ያምነናል? የእግዚአብሔርስ ክንድ ለማን ተገለጠ?” ያለው የነቢዩ የኢሳይያስ ቃል ይደርስ ዘንድ። See the chapter |