Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ዮሐንስ 11:15 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

15 እናንተ እንድታምኑም በዚያ ባለመኖሬ ስለ እናንተ ደስ ይለኛል፤ ነገር ግን ወደ እርሱ እንሂድ፤” አላቸው።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

15 ታምኑ ዘንድ፣ በዚያ ባለ መኖሬ ስለ እናንተ ደስ ይለኛል፤ አሁን ግን ወደ እርሱ እንሂድ።”

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

15 እናንተ እንድታምኑ እዚያ ባለመኖሬ ስለ እናንተ ደስ ብሎኛል፤ አሁን ግን ወደ እርሱ እንሂድ።”

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

15 ታም​ኑም ዘንድ እኔ በዚያ ባለ​መ​ኖሬ ስለ እና​ንተ ደስ ይለ​ኛል፤ ነገር ግን ኑ፥ ወደ እርሱ እን​ሂድ።”

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

15 እንድታምኑም በዚያ ባለመኖሬ ስለ እናንተ ደስ ይለኛል፤ ነገር ግን ወደ እርሱ እንሂድ” አላቸው።

See the chapter Copy




ዮሐንስ 11:15
16 Cross References  

ስለዚህ በክርስቶስ ኢየሰሱስ ያለውን መዳን ከዘለዓለም ክብር ጋር እንዲያገኙ ስል ስለ ተመረጡት ደግሞ ሁሉን ነገር እታገሣለሁ።


እነርሱም ደግሞ በእውነትህ የተቀደሱ እንዲሆኑ እኔ ራሴን ስለ እነርሱ እቀድሳለሁ።”


ኢየሱስም እንዲህ ሲል መለሰ “ይህ ድምፅ ስለ እናንተ መጥቷል እጂ ስለ እኔ አይደለም።


ኢየሱስም ሰምቶ “ይህ ሕመም ለሞት አይሰጥም፤ ይልቁንም ለእግዚአብሔር ክብር መገለጫ ነው፤ የእግዚአብሔር ልጅ በእርሱ ይከብር ዘንድ ነው” አለ።


ኢየሱስ ይህን የምልክቶች መጀመሪያ በገሊላ ቃና አደረገ፤ ክብሩንም ገለጠ፤ ደቀ መዛሙርቱም በእርሱ አመኑ።


ጌታ እንዲህ ይላል፦ ወይን በዘለላው በተገኘች ጊዜ፥ “በረከት በእርሷ ላይ አለና አታጥፉት” እንደሚባለው፥ ሁሉን እንዳላጠፋ ስለ አገልጋዮቼ እንዲሁ አደርጋለሁ።


እነሆ፥ ጥቃት ቢደርስብሽ፥ ከእኔ ዘንድ ግን አይሆንም፤ በአንቺም ላይ የሚነሡ ሁሉ ከአንቺ የተነሣ ይወድቃሉ።


በእግዚአብሔር ልጅ ስም ለምታምኑ፥ የዘለዓለም ሕይወት እንዳላችሁ እንድታውቁ ይህን ጽፌላችኋለሁ።


በብዙዎች በኩል የተትረፈረፈው ጸጋ፥ ለእግዚአብሔር ክብር ምስጋናን እንዲያበዛ፥ ሁሉም ነገር ስለ እናንተ ሆኗል።


የቀባኋቸውን አትንኩ፥ በነቢያቴም ላይ ክፉ አታድርጉ ብሎ፥ ሰው ግፍ ያደርግባቸው ዘንድ አልፈቀደም፥ ስለ እነርሱም ነገሥታትን ገሠጸ።


ዮሴፍ በጲጥፋራ ቤትና ባለው ሀብት ሁሉ ላይ ከተሾመበት ጊዜ ጀምሮ ጌታ የግብፃዊውን ቤት ባረከ፥ የጌታም በረከት በግቢም በውጭም ባለው የጲጥፋራ ሀብት ንብረት ሁሉ ላይ ሆነ።


በዚያችም ሌሊት ጌታ ተገለጠለት፥ እንዲህም አለው፦ “እኔ የአባትህ የአብርሃም አምላክ ነኝ፥ አትፍራ፥ እኔ ከአንተ ጋር ነኝና፥ እባርክሃለሁ፥ ስለ ባርያዬ ስለ አብርሃም ዘርህን አበዛለሁ።”


እንግዲህ ያንጊዜ ኢየሱስ በግልጥ “አልዓዛር ሞተ፤


ዲዲሞስ የሚሉትም ቶማስ ለሌሎቹ ደቀ መዛሙርት “ከእርሱ ጋር እንሞት ዘንድ እኛም እንሂድ፤” አለ።


Follow us:

Advertisements


Advertisements