Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ዮሐንስ 10:38 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

38 የምሠራ ከሆነ ግን፥ እኔን እንኳን ባታምኑ፥ አብ በእኔ እንደሆነ እኔም በአብ እንደሆንሁ ታውቁና ታስተውሉ ዘንድ ሥራውን እመኑ።”

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

38 የማደርገው ከሆነ ግን እኔን ባታምኑኝ እንኳ፣ አብ በእኔ እንዳለ እኔም በአብ እንዳለሁ ታውቁና ታስተውሉ ዘንድ ታምራቱን እመኑ።”

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

38 የአባቴን ሥራ የምሠራ ከሆንኩ ግን በእኔ እንኳ ባታምኑ በሥራዬ እመኑ፤ በዚህ ዐይነት አብ በእኔ እንደ ሆነና እኔም በአብ እንደ ሆንኩ በሚገባ ታውቃላችሁ።”

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

38 ከሠ​ራሁ ግን፥ እኔን እን​ኳን ባታ​ምኑ እኔ በአብ እን​ዳ​ለሁ አብም በእኔ እን​ዳለ ታው​ቁና ትረዱ ዘንድ ሥራ​ዬን እመኑ።”

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

38 ባደርገው ግን፥ እኔን ስንኳ ባታምኑ አብ በእኔ እንደ ሆነ እኔም በአብ እንደ ሆንሁ ታውቁና ታስተውሉ ዘንድ ሥራውን እመኑ።”

See the chapter Copy




ዮሐንስ 10:38
12 Cross References  

እኔ በአባቴ እንዳለሁ እናንተም በእኔ እንዳላችሁ እኔም በእናንተ እንዳለሁ በዚያን ቀን ታውቃላችሁ።


እኔና አብ አንድ ነን።”


ኢየሱስም እንዲህ ሲል መለሰላቸው “ነገርኋችሁ፤ ነገር ግን አታምኑም፤ እኔ በአባቴ ስም የማደርጋቸው ሥራዎች ስለ እኔ ይመሰክራሉ፤


“የእስራኤል ሰዎች ሆይ! ይህን ቃል ስሙ፤ ራሳችሁ እንደምታውቁት፥ የናዝሬቱ ኢየሱስ እግዚአብሔር በመካከላችሁ በእርሱ በኩል ባደረገው ተአምራትና በድንቆች በምልክቶችም ከእግዚአብሔር ዘንድ ለእናንተ የተገለጠ ሰው ነበረ፤


እርሱም በሌሊት ወደ ኢየሱስ መጥቶ “መምህር ሆይ! ከእግዚአብሔር ዘንድ የመጣህ መምህር መሆንህን እናውቃለን፤ እግዚአብሔር ከእርሱ ጋር ካልሆነ በስተቀር አንተ የምታደርጋቸውን እነዚህን ምልክቶች ሊያደርግ የሚችል ማንም የለምና፤” አለው።


እኔ ግን ከዮሐንስ ምስክርነት የሚበልጥ ምስክር አለኝ፤ አብ እንድፈጽመው የሰጠኝ ሥራ፥ ይህ የማደርገው ሥራ፥ አብ እንደ ላከኝ ስለ እኔ ይመሰክራልና።


ከዚህም በኋላ በዓለም አይደለሁም፤ እነርሱ ግን በዓለም ናቸው፤ እኔም ወደ አንተ እመጣለሁ። ቅዱስ አባት ሆይ! እነዚህን የሰጠኸኝ እንደ እኛ አንድ እንዲሆኑ በስምህ ጠብቃቸው።


ኢየሱስም ሰምቶ “ይህ ሕመም ለሞት አይሰጥም፤ ይልቁንም ለእግዚአብሔር ክብር መገለጫ ነው፤ የእግዚአብሔር ልጅ በእርሱ ይከብር ዘንድ ነው” አለ።


ትእዛዙን የሚጠብቅ ሁሉ በእርሱ ይኖራል እርሱም ይኖርበታል፤ በእኛ እንደሚኖር በዚህ እናውቃለን፥ ይኸውም በሰጠን በመንፈሱ ነው።


Follow us:

Advertisements


Advertisements