ኢዩኤል 2:32 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)32 እንዲህም ይሆናል፥ የጌታን ስም የሚጠራ ሁሉ ይድናል፥ ጌታም እንደ ተናገረ፥ በጽዮን ተራራና በኢየሩሳሌም የሚተርፉ ይኖራሉ። ደግሞም ጌታ የጠራቸው ይገኛሉ። See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም32 የእግዚአብሔርን ስም የሚጠራ ሁሉ፣ ይድናል፤ እግዚአብሔርም እንዳለው፣ በጽዮን ተራራና በኢየሩሳሌም፣ መድኀኒት ይገኛል፤ ከትሩፋኑም መካከል እግዚአብሔር የጠራቸው በዚያ ይገኛሉ። See the chapterአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም32 የእግዚአብሔርንም ስም የሚጠራ ሁሉ ይድናል፤ እግዚአብሔርም እንደ ተናገረው ከጽዮን ተራራና ከኢየሩሳሌም መዳን ይገኛል፤ ከሚድኑትም መካከል እግዚአብሔር የጠራቸው ይገኙበታል።” See the chapterየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)32 እንዲህም ይሆናል፤ የእግዚአብሔርን ስም የሚጠራ ሁሉ ይድናል፤ እግዚአብሔርም እንደ ተናገረ፥ በጽዮን ተራራና በኢየሩሳሌም ይድናሉ። ደግሞም እግዚአብሔር የጠራቸው፥ የምሥራች የሚሰበክላቸው ይገኛሉ። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)32 እንዲህም ይሆናል፥ የእግዚአብሔርን ስም የሚጠራ ሁሉ ይድናል፥ እግዚአብሔርም እንደ ተናገረ፥ በጽዮን ተራራና በኢየሩሳሌም መድኃኒት ይገኛል። ደግሞም እግዚአብሔር የጠራቸው፥ የምስራች የሚሰበከላቸው ይገኛሉ። See the chapter |