Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ኢዩኤል 2:18 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

18 ጌታም ስለ ምድሩ ቀና፥ ለሕዝቡም ራራለት።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

18 እነሆ፤ እግዚአብሔር ስለ ምድሩ ይቀናል፤ ስለ ሕዝቡም ይራራል።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

18 እግዚአብሔር ስለምድሪቱ ባለው ቅንአት፥ ለሕዝቡ ራራላቸው፤

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

18 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ስለ ምድሩ ቀና፤ ለሕ​ዝ​ቡም ራራ​ለት።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

18 እግዚአብሔርም ስለ ምድሩ ቀና፥ ለሕዝቡም ራራለት።

See the chapter Copy




ኢዩኤል 2:18
19 Cross References  

የሠራዊት ጌታ እንዲህ ይላል፦ ስለ ጽዮን ታላቅ ቅንዓት ቀንቻለሁ፥ በታላቅም ቁጣ ስለ እርሷ ቀንቻለሁ።


ስለዚህም ከእኔ ጋር ይነጋገር የነበረው መልአክ እንዲህ አለኝ፥ ስበክ፦ የሠራዊት ጌታ እንዲህ ይላል፦ እኔ በታላቅ ቅንዓት በኢየሩሳሌምና በጽዮን ቀንቻለሁ።


አባት ለልጆቹ እንደሚራራ እንዲሁ ጌታም ለሚፈሩት ይራራል፥


በትዕግሥት የጸኑትን የተባረኩ አድርገን እንደምንቈጥር ታውቃላችሁ፤ ኢዮብ እንዴት ታግሦ እንደ ጸና ሰምታችኋል፤ ጌታም በመጨረሻ ያደረገለትን አይታችኋል። ጌታ እጅግ ርኅሩኅና መሓሪ ነው።


ሔት። ያልጠፋነው ከእግዚአብሔር ምሕረት የተነሣ ነው፥ ርኅራኄው አያልቅምና።


ከሰማይ ተመልከት፥ ከቅዱስነትህና ከክብርህም ማደሪያ ጐብኝ፤ ቅንዓትህና ኃይልህስ ወዴት ነው? ለእኔም የሆነው የልብህ ናፍቆትና ርኅራኄህ ለእኔ ተከለከለ?


በጭንቃቸው ሁሉ እርሱ ተጨነቀ፥ የፊቱም መልአክ አዳናቸው፤ በፍቅሩና በርኅራኄውም ተቤዣቸው፥ በቀደመውም ዘመን ሁሉ አንሥቶ ተሸከማቸው።


ተነሥቶም ወደ አባቱ መጣ። እርሱም ገና ሩቅ ሳለ አባቱ አየውና አዘነለት፤ ሮጦም አንገቱን አቀፈውና ሳመው።


በእውነት ኤፍሬም የተወደደ ልጄ ነውን? ወይስ ደስ የምሰኝበት ሕፃን ነውን? በእርሱ ላይ በተናገርሁ ቍጥር አሁንም ድረስ በትክክል አስታውሰዋለሁ፤ ስለዚህ አንጀቴ ታወከችለት ርኅራኄም እራራለታለሁ፥ ይላል ጌታ።


በቁጣዬ ቀሥፌ በፍቅሬ ምሬሻለሁና ባዕዳን ቅጥርሽን ይሠራሉ፤ ነገሥታቶቻቸውም ያገለግሉሻል።


ጌታ እንደ ኃያል ይወጣል እንደ ሰልፈኛም ቅንዓትን ያስነሣል፤ ይጮኻል ድምፁንም ያሰማል በጠላቶቹም ላይ ይበረታል።


የጌታ ጽኑ ፍቅር ግን ከዘለዓለም እስከ ዘለዓለም በሚፈሩት ላይ፥ ጽድቁም በልጅ ልጆች ላይ ነው፥


ከዚያም በመካከላቸው ያሉትን ባዕዳን አማልክት አስወገዱ፤ ጌታንም አመለኩ፤ እርሱም የእስራኤልን መከራ ሊታገሠው የማይቻለው ሆነ።


“የአገልጋዮቹን ደም ይበቀላልና፥ ጠላቶቹንም ይበቀላቸዋልና፥ ምድሪቱንና ሕዝቡን ይክሳልና፥ እናንተ አሕዛብ ሆይ፥ ከሕዝቡ ጋር ደስ ይበላችሁ።”


ጌታ ለሕዝቡ ይፈርዳል፥ ለአገልጋዮቹም ያዝናል። ኃይላቸውም እንደደከመ፥ የታሰረም ሆነ የተለቀቀ እንደሌለ ሲያዩ፥


በባዕዳን አማልክታቸው አስቀኑት፥ በርኩሰታቸውም አስቆጡት።


ከኢየሩሳሌም ቅሬታ፥ ከጽዮን ተራራ ያመለጡት ይመጣሉ፤ የሠራዊት ጌታ ቅንዓት ይህን ያደርጋል።


ከኢየሩሳሌምና ከጽዮን ተራራ የተረፉት ወገኖች ይወጣሉ፤ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ይህን ከመፈጸም አይመለስም።”


Follow us:

Advertisements


Advertisements