ኢዮብ 7:21 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)21 ስለምን መተላለፌን ይቅር አትልም? ኃጢአቴንስ ስለምን አታስወግድልኝም? አሁን በምድር ውስጥ እተኛለሁ፥ ትፈልገኛለህ፥ እኔ ግን የለሁም።” See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም21 መተላለፌን ለምን ይቅር አትልም? ኀጢአቴንስ ለምን አታስወግድልኝም? ትቢያ ውስጥ የምጋደምበት ጊዜ ደርሷል፤ ትፈልገኛለህ፤ እኔ ግን የለሁም።” See the chapterአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም21 ከቶ ኃጢአቴን ይቅር አትልልኝምን? የማደርገውንስ በደል አትደመስስልኝምን? ወደ መቃብር መውረጃዬ ደርሶአል፤ ከእንግዲህ ወዲህ ብትፈልገኝ እንኳ አልገኝም።” See the chapterየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)21 ስለ ምን መተላለፌን ይቅር አትልም? ኀጢአቴንስ ስለ ምን አታነጻም? አሁን በምድር ውስጥ እተኛለሁ፤ በማለዳም አልነቃም።” See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)21 ስለ ምን መተላለፌን ይቅር አትልም? ኃጢአቴንስ ስለ ምን አታስወግድልኝም? አሁን በምድር ውስጥ እተኛለሁ፥ ማለዳ ትፈልገኛለህ፥ አታገኘኝም። See the chapter |