Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ኢዮብ 7:11 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

11 “ስለዚህም ከመናገር አፌን አልከለክልም፥ በመንፈሴ ጭንቀትን እናገራለሁ፥ በነፍሴ ምሬት በኀዘን አንጐራጉራለሁ።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

11 “ስለዚህ ከቶ ዝም አልልም፤ በመንፈሴ ጭንቀት እናገራለሁ፤ በነፍሴም ምሬት አጕረመርማለሁ።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

11 ከእንግዲህ ወዲህ ዝም አልልም! ከመንፈስ ጭንቀቴ የተነሣ እናገራለሁ፤ ከነፍሴ ምሬት የተነሣ አጒረመርማለሁ።

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

11 ስለ​ዚ​ህም እኔ አፌን አል​ከ​ለ​ክ​ልም፤ በመ​ን​ፈሴ ጭን​ቀ​ትን እና​ገ​ራ​ለሁ፤ የነ​ፍ​ሴ​ንም ምሬት በኀ​ዘን እገ​ል​ጣ​ለሁ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

11 ስለዚህም አፌን አልከለክልም፥ በመንፈሴ ጭንቀትን እናገራለሁ፥ በነፍሴ ምሬት በኀዘን አንጐራጕራለሁ።

See the chapter Copy




ኢዮብ 7:11
20 Cross References  

አምላኬ ሆይ፥ ፈቃድህን ለማድረግ ወደድሁ፥ ሕግህም በልቤ ውስጥ ነው።”


“ሕይወቴ ሰለቸኝ፥ የኀዘን እንጉርጉሮዬን እለቅቀዋለሁ፥ በነፍሴም ምሬት እናገራለሁ።


እርሷም ከልቧ ኀዘን የተነሣ ምርር ብላ እያለቀሰች ወደ ጌታ ጸለየች።


እነሆ፥ ታላቅ ምሬት ለደኅንነቴ ምክንያት ሆነ፤ አንተም ነፍሴን ከጥፋት ጉድጓድ አዳንካት፥ ኃጢአቴንም ሁሉ ወደ ኋላህ ጣልህ።


ግን ምን እላለሁ? እርሱ ተናግሮኛል፥ እርሱ ራሱም ይህን አድርጎአል፤ በዘመኔ ሁሉ ስለ ነፍሴ ምሬት ቀስ ብዬ እሄዳለሁ።


ሌላውም ሰው መልካምን ነገር ከቶ ሳይቀምስ በተመረረች ነፍስ ይሞታል።


በብዙ መከራና ከልብ ጭንቀት፥ በብዙም እንባ ጽፌላችሁ ነበር፤ ይህም እናንተን አብዝቼ የምወድበትን ፍቅር እንድታውቁ እንጂ እንዳሳዝናችሁ አይደለም።


በስቃይ ጣር ውስጥ ሆኖ በብርቱ ይጸልይ ነበር፤ ላቡም ወደ መሬት እንደሚንጠባጠቡ የደም ጠብታዎች ሆኑ።


“እኔ ብናገር ሕማሜ አይቀነስም፥ ዝምም ብል ከእኔ አይወገድም።


“ዝም በሉ፥ እናገርም ዘንድ ተዉኝ፥ የፈለገ ነገር ይምጣብኝ።


በደለኛ ብሆን ወዮልኝ፥ ጻድቅም ብሆን ራሴን አላነሣም፥ ጉስቁልናን ተሞልቻለሁና፥ መከራዬንም ተመልክቻለሁና።


ተስፋ የሌለው ሰው ንግግር እንደ ነፋስ ነውና ቃሌን ትገሥጹ ዘንድ ታስባላችሁን?


እርስ በርሳቸውም፥ “ይኸው በወንድማችን ላይ ባደረስነው በደል ምክንያት ቅጣታችንን እየተቀበልን ነው። እርሱ እንደዚያ ተጨንቆ ስለ ሕይወቱ ሲማጠነን፥ እኛ አልሰማነውም ነበር፤ ይህ መከራ የደረሰብንም በዚሁ ምክንያት ነው” ተባባሉ።


ከዝምታ የተነሣ እንደ ዲዳ ሆንሁ፥ ለበጎ እንኳ ዝም አልሁ፥ ሥቃዬም ተቀሰቀሰብኝ።


እኔ፦ የኀዘን እንጉርጉሮዬን እረሳለሁ፥ ፊቴን መልሼ እጽናናለሁ ብል፥


“ዛሬም ደግሞ የኀዘን እንጉርጉሮዬ ገና መራራ ነው፥ በመቃተት ብጮኽም እጁ በእኔ ላይ እንደ ከበደች ናት።


አሁን ከመከራ የምትፈተነው ለዚሁ ነውና፥ ወደ በደል እንዳትመለስ ተጠንቀቅ።


Follow us:

Advertisements


Advertisements