Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ኢዮብ 5:12 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

12 የተንኰለኞችን አሳብ ከንቱ ያደርገዋል፥ እጃቸውም ደባቸውን ከግብ እንዳያደርስ።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

12 እጃቸው ያሰቡትን እንዳይፈጽም፣ የተንኰለኞችን ዕቅድ ያከሽፋል።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

12 ሥራቸው እንዳይሳካ የተንኰለኞችን ዕቅድ ከንቱ ያደርጋል።

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

12 የተ​ን​ኰ​ለ​ኞ​ችን ምክር ይለ​ው​ጣል፥ እጆ​ቻ​ቸ​ውም ቅን አይ​ሠ​ሩም።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

12 እጃቸውም ምክራቸውን እንዳይፈጽም የተንኰለኞችን አሳብ ከንቱ ያደርገዋል።

See the chapter Copy




ኢዮብ 5:12
23 Cross References  

ፍሬአቸውን ከምድር ዘራቸውንም ከሰው ልጆች ታጠፋለህ።


ተመካከሩ፤ ግን አይሳካም፤ ዕቅድ አውጡ፤ ሆኖም አይጸናም፤ እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ነውና።


ያለ ጌታ የሚሠምር፥ ጥበብም የለም፥ ማስተዋልም የለም፥ ምክርም የለም።


የክፉዎች ንድ ትሰበራለችና፥ ጌታ ግን ጻድቃንን ይደግፋቸዋል።


ጴጥሮስም ወደ ልቡ ተመልሶ “ጌታ መልአኩን ልኮ ከሄሮድስ እጅና የአይሁድ ሕዝብ ይጠብቁት ከነበረው ሁሉ እንደ አዳነኝ አሁን በእውነት አወቅሁ፤” አለ።


እኛ ሥራውን ሠራን፤ እኩሌቶቹ ደግሞ ጎሕ ሲቀድ ጀምሮ ከዋክብት እስኪወጡ ድረስ ጦር ይይዙ ነበር።


የጌታም መልአክ ወጣ፥ ከአሦራውያንም ሰፈር መቶ ሰማንያ አምስት ሺህ ገደለ፤ ማለዳም በተነሡ ጊዜ፥ እነሆ፥ ሁሉ በድኖች ነበሩ።


የግብጽም መንፈስ በውስጥዋ ባዶ ይሆናል፥ ዕቅዳቸውንም መና አስቀራለሁ፤ እነርሱም ጣዖቶቻቸውን፥ የሙታን መናፍስትን፥ መናፍስት ጠሪዎቻቸውንና የጠንቋዮቻቸውን ምክር ይጠይቃሉ።


በደልህ ንግግርህን ይመራዋል፥ የተንኰለኞችንም አንደበት ትመርጣለህ።


የሐሰተኞችን ምልክት ከንቱ አደርጋለሁ፥ ምዋርተኞችንም አሳብዳለሁ፥ ጥበበኞቹንም ወደ ኋላ እመልሳለሁ፥ እውቀታቸውንም ስንፍና አደርጋለሁ፤


“እናንተስ፦ ‘ጥበበኞች ነን የጌታንም ሕግ ከእኛ ጋር ነው’ እንዴት ትላላችሁ? እነሆ፥ በውኑ የጸሐፊዎች ሐሰተኛ ብዕር ሐሰት አድርጎታል።


በዚያ ቀን ከኤዶምያስ ጥበበኞችን፥ ከዔሳውም ተራራ ማስተዋልን አላጠፋምን? ይላል ጌታ።


በሦስተኛውም ቀን የያዕቆብ መኮብለል ለላባ ሲነገረው፥


ስለዚህ ዳዊትና ስድስት መቶ የሚሆኑ ሰዎቹ ከቅዒላ ተነሥተው መሄድ ወደሚችሉበት ቦታ ሁሉ ሄዱ፤ ዳዊት ከቅዒላ መሸሹን በሰማ ጊዜ፥ ሳኦል ወደዚያ መሄዱን ተወ።


ነገር ግን ኦርዮ ከጌታው አገልጋዮች ጋር በቤተ መንግሥቱ ቅጽር በር ተኛ እንጂ ወደ ቤቱ አልወረደም ነበር።


አቤሴሎምና የእስራኤል ሰዎች ሁሉም “ከአኪጦፌል ምክር ይልቅ የአርካዊው የሑሻይ ምክር ይሻላል” አሉ፤ ጌታ በአቤሴሎም ላይ ጥፋት ለማምጣት፥ ጌታ መልካም የነበረው የአኪጦፌል ምክር ተቀባይነት እንዲያጣ አድርጎአል።


ኤልሳዕ ግን “ሶርያውያን ደፈጣ አድርገው ስለሚጠብቁህ ወደዚያ ስፍራ አትቅረብ” ብሎ ወደ እስራኤል ንጉሥ ላከ።


እንዲህም ሆነ፥ ጠላቶቻችን በእኛ ዘንድ እንደታወቀ፥ እግዚአብሔርም ምክራቸውን ከንቱ እንዳደረገው በሰሙ ጊዜ፥ እኛ ሁላችንም ወደ ቅጥሩ፥ እያንዳንዳችን ወደ ሥራችን ተመለስን።


የጌታ ዐይኖች እውቀትን ይጠብቃሉ፥ የአታላዩን ቃላት ግን ይገለብጣል።


ስለ ኤዶምያስ፤ የሠራዊት ጌታ እንዲህ ይላል፦ “በውኑ በቴማን ጥበብ የለምን? ከብልሃተኞችስ ምክር ጠፍቶአልን? ጥበባቸውስ አልቆአልን?


Follow us:

Advertisements


Advertisements