ኢዮብ 42:3 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)3 ያለ እውቀት ምክርን የሚሰውር ማን ነው? ስለዚህ እኔ የማላስተውለውን፥ የማላውቀውንም ድንቅ ነገር ተናግሬአለሁ። See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም3 አንተ፣ ‘ያለ ዕውቀት ዕቅዴን የሚያደበዝዝ ይህ ማን ነው?’ አልኸኝ፤ በርግጥ ያልገባኝን ነገር፣ የማላውቀውንና ላስተውለው የማልችለውን ጕዳይ ተናገርሁ። See the chapterአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም3 እኔ የማውቀው በጣም ትንሽ ሆኖ ሳለ ብዙ የምናገረው ለምን እንደ ሆነ ጠይቀሃል። በእርግጥ እኔ ስለማላውቃቸውና እጅግ ድንቅ ስለ ሆነ ነገር ተናግሬአለሁ። See the chapterየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)3 ምክርን ከአንተ የሚሰውር፥ ቃሉንም ከአንተ የሚሸልግና የሚሸሽግ የሚመስለው ማን ነው? የማላስተውለውንና የማላውቀውንም ታላቅና ድንቅ ነገር የሚነግረኝ ማን ነው? See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)3 ያለ እውቀት ምክርን የሚሰውር ማን ነው? ስለዚህ እኔ የማላስተውለውን፥ የማላውቀውንም ድንቅ ነገር ተናግሬአለሁ። See the chapter |