ኢዮብ 42:11 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)11 ወንድሞቹና እኅቶቹ ቀድሞም ያውቁት የነበሩት ሁሉ ወደ እርሱ መጡ፥ በቤቱም ከእርሱ ጋር እንጀራ በሉ፥ ስለ እርሱም አዘኑለት፥ ጌታም ካመጣበት ክፉ ነገር ሁሉ አጽናኑት፥ እያንዳንዳቸውም ብርና የወርቅ ቀለበት ሰጡት። See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም11 ወንድሞቹና እኅቶቹ፣ ቀድሞም ያውቁት የነበሩ ሁሉ ወደ እርሱ መጡ፤ በቤቱም ከርሱ ጋራ ምግብ በሉ። እነርሱም ሐዘናቸውን ገለጡለት፤ እግዚአብሔርም ካመጣበት መከራ ሁሉ አጽናኑት፤ እያንዳንዳቸውም ጥሬ ብርና የወርቅ ቀለበት ሰጡት። See the chapterአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም11 በዚህ ጊዜ የኢዮብ ወንድሞች፥ እኅቶችና ቀድሞ የሚያውቁት ሰዎች ሁሉ ሊጐበኙት መጡ፤ በቤቱም ከእርሱ ጋር ተመገቡ፥ ሐዘናቸውን በመግለጥ እግዚአብሔር ስላደረሰበት ብርቱ መከራ አጽናኑት፤ እያንዳንዳቸውም የብርና የወርቅ ቀለበት ስጦታ አደረጉለት። See the chapterየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)11 ወንድሞቹና እኅቶቹ ቀድሞም ያውቁት የነበሩት ሁሉ የሆነውን ሁሉ በሰሙ ጊዜ ወደ እርሱ መጡ፥ በቤቱም ከእርሱ ጋር እንጀራ በሉ፥ ጠጡም፤ አጽናኑትም፤ እግዚአብሔርም ባመጣበት ክፉ ነገር ሁሉ አደነቁ፤ እያንዳንዳቸውም ጥማድ በሬ፥ አራት ድራህማ የሚመዝን ወርቅና ብር ሰጡት። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)11 ወንድሞቹና እኅቶቹ ቀድሞም ያውቁት የነበሩት ሁሉ ወደ እርሱ መጡ፥ በቤቱም ከእርሱ ጋር እንጀራ በሉ፥ ስለ እርሱም አዘኑለት፥ እግዚአብሔርም ካመጣበት ክፉ ነገር ሁሉ አጽናኑት፥ እያንዳንዳቸውም ብርና የወርቅ ቀለበት ሰጡት። See the chapter |