Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ኢዮብ 38:24 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

24 ብርሃንስ በምን መንገድ ይከፋፈላል? የምሥራቅስ ነፋስ በምድር ላይ እንዴት ይበተናል?

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

24 መብረቅ ወደሚሠራጭበት ቦታ የሚያደርሰው መንገድ፣ የምሥራቅም ነፋስ በምድር ላይ ወደሚበተንበት ስፍራ የሚወስደው የትኛው ነው?

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

24 ብርሃን የሚከፋፈልበት ቦታ ወዴት ነው? ወይስ ደረቅ ነፋስ በምድር ላይ የሚሠራጭበት ቦታ ወዴት ነው?

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

24 አመ​ዳይ ከየት ይወ​ጣል? ከሰ​ማይ በታች ያለ የአ​ዜብ ነፋ​ስስ እን​ዴት ይበ​ተ​ናል?

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

24 ብርሃንስ በምን መንገድ ይከፈላል? የምሥራቅስ ነፋስ በምድር ላይ እንዴት ይበተናል?

See the chapter Copy




ኢዮብ 38:24
7 Cross References  

መብረቅ ከምሥራቅ ወጥቶ እስከ ምዕራብ እንደሚታይ፥ የሰው ልጅ መምጣትም እንዲሁ ይሆናልና፤


ፀሐይም በወጣ ጊዜ እግዚአብሔር የሚያቃጥል የምሥራቅ ነፋስ አዘጋጀ፥ ዮናስ ራሱን እስኪስት ድረስ ፀሐይ ራሱን መታው፤ ለነፍሱም ሞትን ለመነና “ከሕይወት ሞት ይሻላል” አለ።


ብርሃንና ጨለማ እስከሚለያዩበት ዳርቻ ድረስ፥ በውኆች ፊት ላይ ድንበርን አሰመረ።


ይኸውም ለመከራ ጊዜ ለውጊያና ለጦርነት ቀን የጠበቅሁት ነው።


ባድማውንና ውድማውን እንዲያጠግብ፥


ሙሴም በባሕሩ ላይ እጁን ዘረጋ፤ ጌታም ሌሊቱን ሁሉ ጽኑ የምሥራቅ ነፋስ አምጥቶ ባሕሩን አስወገደው፥ ባሕሩንም ደረቅ ምድር አደረገው፥ ውኆችም ተከፈሉ።


Follow us:

Advertisements


Advertisements