Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ኢዮብ 38:18 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

18 ምድርንስ በስፋትዋ አስተውለሃታልን? ሁሉን አውቀህ እንደሆነ ተናገር።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

18 የምድርን ስፋት ታውቃለህን? ይህን ሁሉ ዐውቀህ ከሆነ፣ ንገረኝ።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

18 ዓለም ምን ያኽል ትልቅ እንደ ሆነች ማወቅ ትችላለህን? እስቲ ይህን ሁሉ ታውቅ እንደ ሆነ ንገረኝ።

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

18 ከሰ​ማይ በታች ያለ የም​ድ​ር​ንስ ስፋት አስ​ተ​ው​ለ​ሃ​ልን? መጠ​ኑም ምን ያህል እንደ ሆነ እስኪ ንገ​ረኝ!

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

18 ምድርንስ በስፋትዋ አስተውለሃታልን? ሁሉን አውቀህ እንደ ሆነ ተናገር።

See the chapter Copy




ኢዮብ 38:18
7 Cross References  

ወደ ምድርም ስፋት ወጡ፤ የቅዱሳንንም ሰፈርና የተወደደችውን ከተማ ከበቡ፤ ነገር ግን እሳት ከሰማይ ወርዳ በላቻቸው።


ጌታ እንዲህ ይላል፦ በላይ ያለው ሰማይ ቢለካ፥ በታችም ያለው የምድር መሠረት ቢመረመር፥ በዚያን ጊዜ ስላደረጉት ነገር ሁሉ የእስራኤልን ትውልድ በሙሉ እጥላለሁ፥ ይላል ጌታ።”


አላወቅህም? አልሰማህም? ጌታ የዘለዓለም አምላክ ነው፤ የምድርም ዳርቻ ፈጣሪ ነው፤ አይደክምም፤ አይታክትም፤ ማስተዋሉም አይመረመርም።


አንተ የምድርን ዳርቻ ሁሉ አረጋገጥህ፥ በጋንም ክረምትንም አንተ ሠራህ።


እርሱም የምድርን ዳርቻ ይመለከታል፥ ከሰማይም በታች ያለውን ሁሉ ያያል።


ወደ ዳርቻው ትነዳው ዘንድ፥ ወደ ቤቱም የሚያደርሰውን ጐዳና ታውቅ ዘንድ፥ የብርሃን መኖሪያ መንገድ የት ነው? የጨለማውስ ቦታ ወዴት አለ?


Follow us:

Advertisements


Advertisements