Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ኢዮብ 37:12 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

12-13 ለተግሣጽ ወይም ለምድሩ ወይም ለምሕረትም ቢሆን፥ ሰው በሚኖርበት ዓለም ላይ ያዘዘውን ሁሉ ያደርግ ዘንድ ፈቃዱ ወደ መራቸው ይዞራሉ።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

12 ያዘዘውን ለመፈጸም፣ እርሱ በሚሰጠው መመሪያ፣ በመላው የምድር ገጽ ላይ ይሽከረከራሉ።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

12 ደመናዎች በጌታ መሪነት በምድር ዙሪያ ይዞራሉ፤ የሚያግዛቸውንም ትእዛዞች ይፈጽማሉ።

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

12 እር​ሱም ሰው በሚ​ኖ​ር​በት ዓለም ላይ፥ ያዘ​ዘ​ውን ሁሉ ያደ​ርግ ዘንድ፥ ፈቃዱ ወደ መራ​ችው ይዞ​ራል።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

12-13 ለተግሣጽ ወይም ለምድሩ ወይም ለምሕረት ቢሆን፥ ሰው በሚኖርበት ዓለም ላይ ያዘዘውን ሁሉ ያደርግ ዘንድ ፈቃዱ ወደ መራቸው ይዞራል።

See the chapter Copy




ኢዮብ 37:12
13 Cross References  

እሳትና በረዶ አመዳይና ጉም፥ ቃሉን የሚፈጽም ዐውሎ ነፋስም፥


እነዚህ ትንቢት በሚናገሩበት ወራት ዝናብ እንዳይዘንብ ሰማይን የመዝጋት ሥልጣን አላቸው፤ ውሃዎችንም ወደ ደም ለመለወጥ በሚፈልጉበትም ጊዜ ሁሉ በመቅሠፍት ምድርን የመምታት ሥልጣን አላቸው።


“እኔ ደግሞ መከር ሳይደርስ ገና ከሦስት ወር በፊት ዝናብ ከለከልኋችሁ፤ በአንድም ከተማ ላይ አዘነብሁ፥ በሌላውም ከተማ ላይ እንዳይዘንብ አደረግሁ፤ በአንድ ወገን ባለው መሬት ዘነበ፥ ባልዘነበበትም ወገን ያለው መሬት ደረቀ።


እናንተ የጽዮን ልጆች፥ ጌታ አምላካችሁ ቀድሞ የሚደርሰውን ዝናብ ስለ ጽድቅ ሰጥቶአችኋልና፥ እንደ በፊትም ቀዳሚውንና የኋለኛውን ዝናብ አዝንቦላችኋልና በእርሱ ደስ ይበላችሁ፥ ለእርሱም እልል በሉ።


በውኑ በአሕዛብ ከንቱ ጣዖታት መካከል ዝናብን ሊያዘንብ የሚችል ይገኛልን? ወይስ ሰማይ ካፊያን መስጠት ይችላልን? አቤቱ አምላካችን ሆይ! አንተ አይደለህምን? አንተ እነዚህን ሁሉ ነገሮች አድርገሃልና ስለዚህ አንተን በተስፋ እንጠባበቃለን።


አቤቱ፥ ሥራህ እጅግ ብዙ ነው፥ ሁሉን በጥበብ አደረግህ፥ ምድርም ከፍጥረትህ ተሞላች።


መብረቅን በእጆቹ ይይዛል፥ ያዘዘውንም እንዲመታ ያደርገዋል፥


መብረቁንም ወደ ሰማያት ሁሉ ታች፥ ወደ ምድርም ዳርቻ ይሰድዳል።


መልእክቱን ወደ ምድር ይልካል፥ ቃሉም እጅግ ፈጥኖ ይሮጣል።


እንዳይነሱም፥ ምድርንም እንዳይወርሱ፥ የዓለሙንም ፊት በከተሞች እንዳይሞሉ ስለ አባቶቻቸው በደል ለልጆቹ ሞትን አዘጋጁላቸው።


በሚመጣው ዘመን ያዕቆብ ሥር ይሰድዳል፥ እስራኤልም ያቈጠቁጣል፥ ያብባልም፤ በፍሬያቸውም የዓለሙን ፊት ይሞላሉ።


Follow us:

Advertisements


Advertisements